ሲሲኤስዲ፣ የተማሪዎችን ስኬታማነት ከፍ ለማድረግ፣ የትምህርት ቦታ ደህንነትን ለማጠናከር፣ እንዲሁም በትምህርት ቤት ውስጥ አዎንታዊ ድባብን ለማጎልበት የሚረዳው መሰረታዊ የተማሪዎች የደንብ ልብስ ፖሊሲ አለው። ከሲሲኤስዲ ተማሪዎች የደንብ ልብስ በዋናነት ከሚጠበቁት ጥቂቶቹን እንመልከት። ተማሪዎች መደበኛ ሶል ያለው ጫማ ማድረግ አለባቸው፤ የፀሐይ መነፅር በትምህርት ቤት ውስጥ ማድረግ አይፈቀድም፤ ቁምጣዎች፣ ጉርድ ቀሚሶች ወይም መደበኛ ቀሚሶች ቢያንስ እጃችንን ወደ ታች ዘርግተን ስንቆም የመሃል ጣታችን ጫፍ ድረስ መርዘም አለባቸው፤ ኮፍያ ወይም ቆብ በትምህርት ቤት ውስጥ ማድረግ አይፈቀድም፤ እንዲሁም የውስጥ ልብስና ከደረት እስክ ዳሌ ያለው የሰውነት ክፍል መታየት የለበትም።