የትምህርት ቤት ምግቦች

School Meals

የምግብ ገደቦች

ልጅዎ እንደ አሳማ፣ ጄላቲ፣ ዓሳ የመሳሰሉ የምግብ አይነቶች እንዳይመገብ ገደብ ካለበት ለትምህርት ቤቱ ቢሮ እና ለአስተማሪው ማሳወቅ አለብዎ። በተጨማሪ የየወሩን የሲሲኤስዲ የምግብ ዝርዝር ከሲሲኤስዲ የምግብ አገልግሎት ማግኘትና ማጣራት ይችላሉ፤ ወይም ከቤትዎ ምግብ ማምጣት ይችላሉ።

ልጅዎ ለማንኛውም ምግብ አለርጂ ከሆነ፣ ከሐኪምዎ ማስታወሻ ማግኘት አለብዎ። በተማሪዎች የሕክምና ፈቃድ ቅጽ ላይ ልጅዎ አለርጂ የሆነባቸውን ነገሮች ዝርዝር ማስፈርዎን እርግጠኛ ይሁኑ።

የመካከለኛ ትምህርት ቤት፣ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የምግብ ዝርዝርን በቀጥታ ለማየት ይህን ጽሑፍ ይጫኑ

ማመልከቻ

የክላርክ ካውንቲ ዲስትሪክት በብሔራዊ የትምህርት ምሳ/ቁርስ መርሃ ግብር በሚሳተፉ የመጀመሪያ ደረጃ፣ መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ እና የቤተሰብ ብዛትና የገቢ መጠን መስፈርትን ለሚያሟሉ የተወሰኑ ተማሪዎች፣ በእያንዳንዱ የትምህርት ቀን ምግብ በቅናሽ ያቀርባል።

የነጻ ወይም ቅናሽ ምግብ ተጠቃሚዎች ማመልከቻ በየዓመቱ መሞላት ያለበት ሲሆን፣ ለአንድ ቤተሰብ አንድ ማመልከቻ ብቻ ነው የሚያስፈልገው። ማመልከቻውን ለማስተናገድ 10 የሥራ ቀናት ይወስዳል። ማመልከቻውን በሚከተለው ድረገጽ ላይ በኦንላይን እንዲያመለክቱ እናበረታታለን፡ https://www.fns.usda.gov/documents-available-other-languages ምክንያቱም ይህ አማራጭ ለተጠቃሚው ምቹ ከመሆኑ በተጨማሪ የማመልክቻውን የማስተናገጃ ጊዜ ይቀንሳል። ማመልከቻዎች የሚስተናገዱት በዋናው የምግብ አገልግሎት ቢሮ ውስጥ ሲሆን፣ አንድ ተማሪ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን የሚጀምረው፣ መስፈርቱን ማሟላቱ ከተረጋገጠ በኋላ ነው።

በትምህርት ዓመቱ መጨረሻ የቅናሽ ምግብ መርሃ ግብሩን መስፈርት ያሟሉ ተማሪዎች ተጠቃሚነታቸው እስከ ሴፕተምበር 25 ቀን 2018 የሚቀጥል ይሆናል። ከሲሲኤስዲ የምግብ አገልግሎት መምሪያ የልጅዎን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥና ለ2018-2019 የትምህርት ዓመት ብቁ መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ ካላገኙ በስተቀር የ2018-2019 የነጻ ወይም ቅናሽ ምግብ ማመልከቻ ማስገባት አለብዎ።