በጋ (ሳመር) ተማሪዎች ትምህርትን የሚቀጥሉበት ጥሩ ጊዜ ነው! በትምህርት ዓመቱ ውስጥ ሲካሄድ በነበረው ትምህርት ላይ ተማሪዎች እና ቤተሰቦች እንዲገነቡ ለመርዳት DPS ተማሪዎችን በበጋው ወቅት በሞላ በትምህርት ላይ እንዲቆዩ በማድረግ ላይ በማተኮር የትምህርት መረጃ/ግብዓት ክምችቶችን አዘጋጅቷል። አብዛኛዎቹ መረጃዎች/ግብዓቶች የተዘጋጁት ከአጸደ ሕፃናት እስከ 5ኛ ክፍል ድረስ ላሉ ቢሆንም ለሌሎች ክፍሎች ጥቂት መረጃዎች/ግብዓቶች ይገኛሉ። ይህ ዝርዝር አዳዲስ መረጃዎች/ግብዓቶች እንደተገኙ የሚታከሉበት በመሆኑ እየተመለሱ ይመልከቱ።
StoryBird (Multiple Languages) በቀላሉ መጠቀም የሚቻል መሳሪያ ሲሆን ተማሪዎች የሚያምሩ የጽሑፍ ታሪኮችን እንዲፈጥሩ ያደርጋል። ተማሪዎች በታሪኮች ላይ መተባበር ይችላሉ።
SpeakPipe ድምጽ መቅጃ የድምጽ ቅጂዎችን በቀጥታ ከአሳሽ ላይ በማይክሮፎንዎ እንዲቀዱ ያስችሎታል። ቅጂው የሚቀመጠው እዛው ኮምፒተርዎ ላይ ስለሆነ የሚፈልጉትን ያህል ጊዜ መቅዳት ይችላሉ። ቅጂዎን በ SpeakPipe ሰርቨር ላይ የሚያስቀምጡበት እና ማያያዣ የሚያገኙበት አማራጭ አለ፣ ይህም በኢሜይል እንዲልኩት ወይም በድረ ገጽ እንዲጠቀሙት ነው።
Duolingo (Multiple Languages) ኦንላይን ፕሮግራም ሲሆን ነፃ ትምህርቶችን እና መማሪያዎችን በእንግሊዘኛ፣ ስፓኒሽ፣ ፍሬንች፣ ጀርመን፣ ጣሊያንኛ፣ ፖርቹጊዝ፣ ግሪክ፣ ሩሲያኛ፣ ቪዬትናሚዝ፣ እና ሌሎችን ጨምሮ በተለያዩ ቋንቋዎች ያቀርባል። ዕለታዊ ልምምዶች ሰዋሰው እና ስነ ቃላት የሚያጠቃልሉ ሲሆን የቋንቋ ዕውቀትን ለመገንባት የተቀረፁ ናቸው።
K-12 DPS Ebook Library (SORA) (Multiple Languages) - ት/ቤት በሚዘጋበት ወቅት፣ Denver የሕዝብ ት/ቤቶች ነጻ የ Sora ኢመጽሐፍ እና የድምጽ መጽሐፍ መዳረሻን ለሁሉም የ DPS ተማሪዎች እና ሰራተኞች ያቀርባል፣ የቻርተር ት/ቤት ኔትወርክ ጨምሮ። ተማሪዎች እና ሰራተኞች 30,000 ኢመጽሐፎችን እና የድምጽ መጽሐፎችን በ DPS ማስረጃዎች በመግባት በማንኛውም ኮምፒዩተር፣ ታብሌት ወይም ስማርት ስልክ ወዲያው መድረስ ይችላሉ።
K- 12 Denver Public Library (Multiple Languages)- ኦንላይን ይሳተፉ፡ የመጽሐፍ ክለቦች፣ የታሪክ ጊዜዎች፣ የመጽሐፍት መዝናኛ እና የቤተ መጻሕፍት አገልግሎቶች ከቤትዎ።
3- 12 Commonlit.org (Multiple Languages) ለትርፍ ያልተቋቋመ የትምህርት ቴክኖሎጂ ድርጅት ሲሆን ሁሉም ተማሪዎች፣ በተለይ Title I ት/ቤቶች ውስጥ ያሉ ተማሪዎች፣ በኮሌጅ እና ከዚያም በላይ ውጤታማ ለመሆን የሚያስፈልጋቸውን የማንበብ፣ የመፃፍ፣ የግንኙነት፣ እና ችግር የመፍታት ክህሎቶች ይዘው መመረቃቸውን ያረጋግጣል።
Math Learning Center Family Resource (Multiple Languages) ት/ቤቶች ሊዘጉ ይችላሉ፣ ሒሳብ መማር ግን ይቀጥላል! ከቤት ለመማር ነጻ መርጃዎችን እናቀርባለን።
6-8 grade: Connected Mathematics - ለተማሪ የሒሳብ ስራዎችን ያቀርባል።
K-2- National Council Teachers Mathematics - The National Council of Teachers of Mathematics (የሒሳብ መምህራን ብሔራዊ ምክር ቤት) ለእያንዳንዱ ተማሪ ከፍተኛ ጥራት ያለው የሒሳብ ማስተማር እና መማርን ይደግፋል።
Youcubed (Multiple Languages) - ተማሪዎች ከ CMP3 ጋር በዓመቱ ካጠናቀቋቸው ትምህርቶች ጋር ከሚዛመዱ ጨዋታዎች እና ተንቀሳቃሾች ጋር ቨርቱዋሊ መስተጋብር ማድረግ ይችላሉ።
Khan Academy (Multiple Languages) ተማሪዎች በክፍል ደረጃ የሒሳብ ኮርስ ክህሎቶችን መመልከትና መለማመድ ይችላሉ።
በቅርብ ቀን የሚመጣ
ልዩ የትምህርት መርጃዎቹ ተማሪዎች በሰመር ወቅት እንዲማሩ ዕድሎችን ያቀርባሉ።
Community Resources - በማህበረሰብ ውስጥ የሚከተሉትን አገልግሎቶች የሚያቀርቡ አጋሮች፦ ጤና፣ የአካል ብቃት፣ ደህንነት፣ ስለ ገንዘብ ነክ ነገሮች መማሪያ፣ ስቴም፣ ሰዕል፣ ቱተሪንግ፣ ማብሰል፣ መምራት፣ ትምህርታዊ ድጋፍ፣ ምክር፣ ተሟጋችነት፣ ቴራፒ።
Summer Meal Program 2020 Distribution Sites- Summer Food Service Programs (ሰመር የምግብ አገልግሎት ፕሮግራሞች) ለሁሉም ተማሪዎች የተመጣጠነ ቁርስ እና ምሳ ያቀርባሉ።
የበጋ ትምህርት አስደሳች ተግባሮች (መልመጃዎች)- ይህ መርጃ የልጅን የመማር ችሎታ እና የሰመር እንቅስቃሴዎች እንዴት መደገፍ እንደሚቻል ልዩ ፍላጎቶች የሚያስፈልጋቸውን ጨምሮ ለሁሉም ቤተሰቦች ጠቃሚ ምክሮችን ይሰጣል።