Profile

እናስተዋውቃችሁ፤

መግቢያ

የርዕሰ አድባራት ሎንደን ደብረ ጽዮን ቅደስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሕንጻ ተገዝቶ ካለቀ በኃላ ሕንጻውን መሠረት ባደረገ ግለሰባዊና የቡደን ፈላጎት ሎንደን ቅድሥት ማርያም ኃፊቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ በማድረግ ሕዝበ ከርስቲያኑ ሳያውቀው በደብቅ ያስመዘገቡና የንብረት በአለቤትነት የምስክር ወረቀት ከመያዛቸውም በላይ ምዕመናኑን በመክፋፈል በቤተክርስቲያን ውስጥ አመጽ በማስነሳት ቤተ ክርስቲያንን ያዘጉ ዋና ዋናዎቹ ገጽ ባህርያትን ከዚህ እንደ ሚከተለው እናስተዋውቃችሁ ።

1ኛ) ጌታቸው በሻህውራድ

በኢሀፓ ውስጥ መጠነኛ አገልግሎት የሰጠ በአካውንታት ሥራ የሚተዳደር፣ በቤተ ከርስቲያኑ ውስጥ የቁጥጥር ኮሚቴ ሆኖ የሰራ በሕግ ማርቀቁ ሥራ ውጥ ሳይመረጥ እራሱን ኮሚቴ አደርጎ የሰየመ፣ ቤተ ክርስቲያኑን ከሕገ ከቤተ ክርስቲያን ውጪ አስወጥቶ በካንፓኒ እንደተመዘገብ ከፍተኛ ደባ የፈጸመ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ የበላይነት የማያምንና የቤተ ክርስቲያንን ሕልውና የሚፈታተን፤ ሰዎችን ማለቂያ ወደሌለው የስህተት ጎዳና የመራና በየቀኑ ቃሉን የሚለዋውጥ። ወጣቶችን በወደፊት የተስፋ ዳቦ እያደነዘዘ አእምሯቸውን እየተቆጣጠረ ባሳደጓቸው ካህናት መንፈሳዊ አባቶቻቸው ላይ አመጽ የሚያስነሳ፣ እራሱን የሎንደን ቅድሥት ማርያም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ አካውንታንት አድርጎ የተሾመ።

2ኛ) ሻለቃ ማሞ ለማ

በደርግ ሥርዓት ውስጥ በደህንነትና በጆሮ ጠቢነት ሲያገለግል የኖረ በአሁኑ ስዓት በጡረታ የሚገኝ ቤተ ክርስቲያኑ በካንፓኒ ሕግ እንድትመራ ከፈተኛውን አስተዋጽዖ ያደረገ ካህናትን የሚሳደብ ወደ ቤተ ክርስቲያን ከነጫማው የሚገባ በቤተክርስቲያን ውስጥ አመጽ ያሰነሳና ጽሎት ክርስትና እና ቅዳሴ እንዲቋረጥ ያደረገ፤ ብጹዓን ሊቃነጳጳሳት ቤተክርስቲያን ለመክፈት ሲመጡ ሰላምዊ ሰልፉን የመራ በግንቦት ሰባት በሚባለው የፓለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ በወታደራዊ አማካሪነትና አሰልጣኝነት የሚያገለግል፤

3ኛ) ዘላለም ተሰማ

የግንቦት ሰባት የፓለቲካ እንቅስቃሴ ሥራ አስፈጻሚ እና የኢሳት ቴሌቪን ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ በሎንደን ቤተ ክርስትያን ኃላፊነቱ በተወሰነ የግል ኩባንያ እንድትመራ ከፍተኛ ጥረት የሚያደረግ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከምነታችን ወጪ የሆኑትን የ እስልምና ተከታዮችን ሁሉ በማሰባሰብ ኪዳን እየደረሰ ቅዳሴ እየተቀደሰ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ካህናትን በቮት ኦፍ ኖ ኮንፊደንስ አውርደናል በማለት የሚሳደብ፤ ቄስ ብርሃኑ ብሥራትን በራሱ ሥልጣንና ፊርማ የርዕሰ አድባራት ሎንደን ቅደስት ማርያም ኃላፊንቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ አስተዳዳሪ አድርጎ የሾመ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የማያባራ አመጽ በማሰንሳት ቤተ ክርስቲያኑ እንዲዘጋ ያደረገ።

4ኛ) ጥላዮ የሻነው

ጌታቸው በሻህውረድ የተናገረውን ተከትሎ የሚሳብ በራስ የመተማመን፣ የመረዳትም ሆነ የማስረዳት ችግር ያለበት ያለካህናትና ምዕመናን ምርጫ ያለሰባካ ጉባዔ ውሳኔ ከአቶ ግርማ ተሊላ ጋር በመሆን ያስመዘገብ የለንደን ደብረ ጽዮን ቅደስት ማርያም ኃልፊነቱ የተውሰነ የግል ኩባንያ ምክትል ዴሬክተርና የካንፓኒው ዋና ጸሐፊ በመሆን የቤተክርስቲያን ሕንጻ ባለቤት ለመሆን ከፈተኛ ሙከራ ያደረገ።

5ኛ) አቶ ግርማ ተሊላ

በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኤሌክትሪሻንነት ያገለገሉ በሎንደን ቅደስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በቅንነት ሲያገለግሉ ሲታዘዙ የቆዮ ቅን የቤተ ክርስቲያን ሰው ነበሩ ነገር ግን ከግዜ በኃላ ጌታቸው በሻህውራድ ባውጠነጠነው የቤተ ክርስቲያን ንብረት ባለቤትነት ሴራ ውስጥ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የገቡ በመጨረሻም ቤተ ክርስቲያን ኃላፊነቱ በተወሰነ የግል ኩባንያ ያሰመዘገበና የሎንደን ደብረ ጽዮን ቅደስት ማርያም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ዋና ዴረክተር የሆኑ።

6ኛ) ስዩም ደምሴ

በካንፓኒ ረቂቅ ላይ የተሳተፈ አለሁበት! ሌላ ጊዜ የለሁበትም! የሚል ቤተ ክርስቲያን ወደ ካንፓኒ እንድትለወጥ በአጋፋሪንት የሚያገለግል አቋም የሌለው ነገሮችን አቀጣጥሎ የማይገኝ፤ ከሀገር ቤት በሚመጡት እንግዶች ካህናት ላይ የሚያሳምጽና ድንጋይ የሚያስወረውር፤ ጳጳሳት ሲመጡ መስቀል አትሳለሙ የሚለና ጀርባውን የሚሰጥ ታማኝነት የሌለው ወላዋይ ለጽድቅም ለሃጥያትም የማይመች፣ ለእውነትም ለውሸትም የማይስማማ የሁለት ዓለም ስደተኛ በጊዚያዊነት መስሎ አዳሪ።

7ኛ) አቶ ተሾመ ሰይፉ

እግዚአብሔርን ፈሪ ሰውን አክባሪ፣ጥሩ አማኝና የቤተ ክርስቲያን ሰው የነብሩ፤ ነገርግን የህታቸው ባል ጌታቸው በሻህውረድ የተናገረውን ሁሉ መልአክ እንደተናገረው ሁሌም ትክክል ነው ብለው የሚቀበሉ የካንፓኒው ሕግ ሲረቀቅ በሰብሳቢነት ያስረቀቁ ቤተ ክርስትያን በካንፓኒ እንድትመዘገብ ያደረጉ፡ጌታቸው በሻህውረድን ማንም ሳይመርጠው የካንፓኒ አርቃቂ ዋና አባል ያደረጉ እሱን በማመን ብቻ ለዚህ ሁሉ ብልሽት ምክንያት የሆንኑ።

ማጠቃለያ፤

እነዚህ ከዚህ በላይ ስማቸው የተዘረዘርው ግለሰቦች በአውሮፓ ቀደምት የሆነችው የርዕሰ አደባራት ሎንደን ደብረ ጽዮን ቅደስት ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከቅዱስ ሲኖዶስ የበላይነት፤ በእንግሊዝ ሀገር በጎአደራጎት ድርጂት( ከቻሪቲ ኮሚሽን) አስተዳደር አስወጥተው፤ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ በግልና በቡድን በረቀቀ ስልት በባለቤትነትና በርስት ጉልትነት ለመያዝ ሲሉ ብቻ በቤተ ክርስትያኑ በሕንጻው ስም ባንክ ለመበደር፣ በወለድ አገድ ለማስያዝ፣ ከሌሎች የገንዘብ አትራፊ ድርጂቶች ጋር ሽርክና ለመግባት(ሼር) በሚያስችላቸው መልኩ የአጥቢያው ማህብረ ካህናት ማህብረ ምዕመናን ሳያውቀው ሰበካ ጉባኤ ሳይወስን በደብቅ ሎንደን ቅደስት ማርያም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ አድርገው ከማስመዝገባቸውም በላይ ፤ ይህ ተግባራዊ ሳይሆን ስለቀረ ብቻ ለቤተ ክርስትያን ተቆርቋር በመስል እራሳቸውን ከሊቃነ ጳጳሳቱ በላይ በመሾም፣ ምዕመናንን በመክፋፈል ፣ ለጸብን በማነሳሳት፣ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሰላምዊ ሰልፍ በማድረግ፣ ምዕመናን በጎሳ በመለያየት ካህናትን በመሳደብና መንፈሳዊ አገልግሎቱ በኃይል እንዲቋረጥ አድርገው ያዘጉ፤ ብጹዓን ሊቃ ጳጳሳት ሲመጡ አመጽ የሚያስነሱ በሲኖዶስ የበላይ መንፈሳዊ አስተዳደር የማያምኑ ግለሰቦች፤ ድብሩን፣ካህናቱንና ም ዕመናኑን በመጥፎ ስም የሚያስጠሩ እንዳ ተቀባይ ያለሆኑ በመሆናቸው በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ በተፈጠረው ችግር በኃላፊነት በእግዚአብሔርም፣ በታሪክም፣ በሰውም፣ በሕግም መጠየቅ ያለባቸው ግለሶች ናቸው።

ለበለጠ ማስረጃ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚቀርበውን፡

ቤተ ክርስቲያንን ካንፓኒ አደረገው ያሰምዘገቡበትን፤

ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በየጊዜው የሚያስነሱትን አመጽ የቪዲዮ ማስረጃ ይመልከቱ፤

ዜና ደብረ ጽዮን ድህረገጽ ገብተው የተጻፉትን እውነተኛ መረጃዎችና ዜናዎች ያንብቡ፤

ሀናቱንም ሆነ እውነተኛ ምዕመናን ቀርበው በመጠየቅ እውነቱን ይጠይቁ ፤ይረዱ፡