Post date: Dec 11, 2013 5:51:09 PM
ዜና ደብረ ጽዮን ዕለቱ ኅዳር 25 ቀን 2006 ዓ.ም
ከሳምንት እስከ ሳምንት
አርስተ ዜና
v በርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድሥት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሕንጻ ባለቤትነት ይገባኛል ጥያቄ በማንሳት መንፈሳዊ አገልግሎት በኃይል አቋርጠው ቤተ ክርስቲያኑን በአመጽ ያዘጋው የእነጌታቸው በሻህውረድ የደጀ ሰላም አማጺ ቡድን ከ£60,000 (ስልሳ ሺህ ፓውንድ በላይ ለጠበቃ እና ለልዩ ልዩ ወጪዎች ግንዘብ ማባከኑ ይፋ ሆነ፤
v መልአከ ጽዮን አባ ግርማ ከበደ(ቆሞስ) የርዕሰ አድባራት ሎንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ቤተ ክርስቲያኑ በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ የተመሠረተበትን ሃይማኖታዊ፣ ሕጋዊ ባለቤትነትን የሚያረጋግጥና ሌሎችም ታሪካውዊ ሰነዶችን እና ማስረጃዎችን በመያዝ ከኢትዮጵያ ወደሚኖሩበት እንግሊዝ ሀገር በሰላም ተመለሱ፤
v ቻሪቲ ኮሚሽ ሰበካ ጉባኤው ቻሪቲውን/ ቤተ ክርስቲያኑን/ በኃላፊነት የማንቀሳቀስ እና ምርጫውን የማስፈጸም መብትና ሕጋዊ ሥልጣን እንዳለው ማረጋገጫ ሰጠ፤
ዜና በዝርዝር
በቤተ ክርስቲያን ሕንጻ ባለቤትነት ጥያቄ ከአንድ ዓመት በላይ በአመጽ ላይ የቆየው የእነጌታቸው በሻህውረድ የደጀ ሰላም አማጺ ቡድን ቤተ ክርስቲያኑን በካንፓኒ ስም አስመዝግበው በግል ባልቤትነት ለመረከብ እና ካህናትን ለማባረር ከ£42,000 በላይ ለጠበቃ ከ£8,000 ለአዳራሽ ፣£12,000 በላይ ለልዮ ሉዩ ወጪዎች እና ለነቄስ ብርሃኑ ብሥራት ደመውዝ በደምሩ £62,000 በላይ ወጭ እንዳደረገ ዲሴምበር 1 ቀን 20013 ባደረገው ስብሰባ ላይ ከቀረበው ሪፓርት ለመረዳት ተችልዋል።
ይሁን እንጅ ይህ ሁሉ በቤተ ክርስቲያን ስም ተሰብስቦ አላግባብ ወጭ የሆነው ገንዘብ ምንም ወጤት ያለመጣና በጠበቃቸው ከዌለርስ ግሩፕ በኩል ምን ዓይነት ሥራ እንደተሰራ ሕንጻውን በባለቤትነት ለመረከብ መቻሉን ወይም አለማቻሉን በጠቅላላው እንቅስቃሴው ምን ደረጃ ላይ ደርሶ እንደቆመ የሚገልጽ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው ሪፓርት አለመቅረቡ የዜና ክፈላችን ያቀረበው ዘገባ ያስረዳል ።
በዚህም ምክንያት የችግሩ አሳሳቢነት ያስጨነቃቸው አንዳንድ ክርስቲያኖች፤ እነጌታቸው በሻህውረድ በጭፍን አስተሳሰብ የምዕመናን ገንዘብ አለአግባብ ማባከን እና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተፈጸመው አመጽ ሁሉ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ የሚያመዝን መሆኑን በመረዳት ተጨማሪ ስህተት ላለመሥራት ቆም ብሎ ወደኃላ ማሰብ እንደሚገባ ቅንነት የተሞላው እና ክርስቲያናዊነት የተላበሰ ሐሳብ ቢያቀርቡም፤ በዘላለም ተሰማ እና በቄስ ብርሃኑ ብሥራት እንዲሁም በሌሎቹ የካንፓኒ ሰዎች እና «ጨቅላ ፓለቲከኞች» አማካኝነት ሐሳባቸው ተቀባይነት ካለማግኘቱም በላይ ግለሰቡ ላይ ሥርዓት አልበኝነት የተላበሰ ነቀፌታ የደረስባቸው መሆኑ ወስጥ አዋቂ የዜና ምንጫችን ዘግቧል። በተቃራኒው የሕዝብ ገንዘብ አላግባብ ላባከኑት ለጌታቸው በሻህውረድና ተባባሪዎቹ የድጋፍ ጭብጨባ የተቸራቸው መሆኑን ከዘገባው ለመረዳት ችለናል።
በሌላ በኩል የተቃውሞ ሐሳቡን ያቀረቡትን ግለሰብ ድጋፍ የሚሰጡ አንዳንድ አባላት እነቄስ ብርሃኑ ገንዘብ እስከተክፈላቸው ደረስ ስለቤተ ክርስቲያኑ መዘጋት እና ስለምዕመናን መጉላላት ደንታ የሌላቸውም በማለት ቅሬታቸውን ከመግለጻቸውም በላይ «እባከዎት ቤተ ክርስቲያኑ ይክፈቱልን» በማለት በስልክ የጽሁፍ መልዕክት ለእነ አባ ግርማ ከበደ እየላኩ መሆናቸውን የዜና ክፍላችን ያጠናክረው ሪፓርት ያስረዳል።
እነ ጌታቸው በሻህውረድ ያለ ሰበካ ጉባዔው ፈቃድ እና እውቅና በአመጽ በቤተ ክርስቲያን ስም ጥሪ እያደረጉ ገንዘብ አሰባሰበዋል፤ ዛሬ አላግባብ የሚባክነው የቤተክርስቲያን ገንዘብ በዚህ መልኩ ጥሪ እያደረጉ ነበር የሰበሰቡት። ይህ የምታዩት የጥሪ ካርድ ሕገውጥ ነው። ሕግ በማስረጃነት የሚፈልገው ሕገወጥ ተግባር ነው። አሁንም ይህንኑ ሕገወጥ ተግባር አሁንም ቀጥለውበታል።
መላአከ ጽዮን አባ ግርማ ከበደ ወደ ትውልድ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ሂደው ሁለት ሳምንታት ያክል ቆይታ ካደረጉ በኃላ በሰላም ተመልሰዋል። መላአከ ጽዮን አዲስ አበባ በቆዩበት ስዓት ወደ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት በመሄድ በቋሚ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ በአካል ተገኝተው በርዕሰ አድባራት ሎንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ጥቂት ግለሰቦች የሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ የግል ባለቤት ለመሆን ባስነሱት አመጽ ምክንያት በመንፈሳዊ አገለግሎቱ የደረሰውን በደልና በመጨረሻም ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ቤተ ክርቲያኑን መዘጋቱን ሪፓርት ማደገጋቸውን ለደብሩ ካህናት፣ምዕመናን ወጣቶች መግለጫ የሰጡ መሆናቸን የዝግጅት ክፍላችን ዘግቧል።
ቋሚ ሲኖዶስ ጉዳዮን በአጀንዳ ይዞ የተወያየበት ቢሆንም ምን ወስኔ እና መመሪያ እንደሰጠ እስካሁን ይፋ የሆነ ነገር አለመኖሩ ታውቋል፤ የዚህ ዜና እንደደረሰን በቅርቡ ዘገባችን በበቂ ማስረጃ አጠናክረን ይዘን እንቀርባለን።
መልአከ ጽዮን አባ ግርማ በቅዱስ ፓትርያርኩ ትእዛዝ ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያኑ መሥራች እና ሕጋዊ ባለቤት መሆኑን የሚገልጽ ጠቃሚ የሆነ ማስረጃዎችን ያመጡ መሆናቸውን ለደብሩ አስተዳደር ቅርበት ያላቸው የዜና ወኪላችን ሪፓርት ያሰረዳል። በተጨማሪም የመጀመሪያው አስተዳዳሪ አባ አረጋዊ ወልደ ገብርኤል/አቡነ ዮሐንስ በብጹ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ፓትርያርክ ተሹመው ሲመጡ ለእንግሊዝ መንግሥት፣ ለአንገሊካን ቤተ ክርስቲያን፣ ለአርመንያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በእንግሊዝ፣ ለሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በእንግሊዝ ለአገልግሎታችው መቃናት እና በማንኛውም ነገር ሁሉ ትብብር እንዲደረግላቸው የዛሬ አርባ ዓመት የተጻፉና በፓትርያርኩ የተፈረሙ ታሪካዊ ማሰረጃዎችን አምጥተው ለጽህፈት ቤቱ ገቢ ማደረጋቸው ተረጋግጧል። እነዚህ ሰነዶች ለማንኛውም ሕጋዊ ክትትል አስተማማኝ መረጃዎች እንደሚሆኑ የሕግ ባለሙያዎች የሰጡትን ሐሳብ የዜና ወኪላችን ጨምሮ ዘግቧል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ ዜና አባታችን አባ አረጋዊ/ ብጹዕ አቡነ ዮሐንስ ከስተዳዳሪነት ጅምሮ እስክ ጵጵስና እና እስከለተ እረፍታቸው ድረስ ከብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ፤ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፤ አቡነ መርቆሬዎስ እና ከአቡነ ጳወሎስ ከአራቱም ፓትርያርኮች ጋር ሰላማዊ የሆነ መለካም መንፈሳዊ የሥራ ግኑኝነት እንደነበራቸው መ/ጽ አባ ግርማ ከበደ ካመጧቸው ን ታሪካዊ ሰነዶችን በአካል ለማየት የተቻለ መሆኑን የዜና ወኪላችን ዘግቧል።
በተቃራኒው እነኮማንደር አሰፋ «የእንቁላል ጦረኞች» ብጹዕነታቸውን አቡነ ዩሐንስን የከሰሱበትና ስማቸውን ያጠፉበት አሳዛኝ እና አሳፋሪ ደብዳቤዎችንም እንደተመልከተ ገልጾ፤ እነዚህን ደብዳቤዎች ያዩ ግለሰቦች አባ ግርማ ከበደ የአባቶቻቸው የመካራ ጽዋ ተካፋይ በመሆናቸ እድለኛ ናቸው በማለት አስተያየት የሰጡ ተመልካቾች እንደነበሩ የቀረበው ዘግባ ያስረዳል። ሁሉንም ደብዳቤዎች በቅርብ ቀን በዜና ደብረ ጽዮን ድህረ ገጽ ይፋ የምናደርግ መሆኑን ቃል እንገባለን።
ቤተ ክርስቲያኑን በእንግሊዝ ሀገር ሕግና ደንብ መሠረት በስሟ መዘግቦ በባላደራዎች እያስጠበቀ የሚገኘው የቻሪቲ ኮሚሽን በ2007 የተመረጠው እና በ2010 በጠቅላላ አባላቱ ድምጽ የሥራ ዘመኑ የተራዘመለት ሰበካ ጉባኤ ወይም ትረስቲ/ ቤተ ክርስትያኑን በኃላፊነት የመምራት የታዮትን ለዩነቶች በስምምነት በመፍታት አዲስ የሰበካ ጉባኤ የማስመረጥ ኃልፊነት እንዳለው ማረጋገጫ የሰጠ መሆኑን ሪፓርተራችን ቻሪቲ ኮምሽን የጻፈውን ደብዳቤ ዋቢ አደርጎ ያቀረበው ዘግባ ያሰረዳል። ቻሪቲ ኮሚሽኝ ምርጫ በሚካሄድበት ወቅት ታዛቢ ደርጅቶችንም ጥቆማ ያደረገ መሆኑን ተዘግቧል።
ዘገባው እንደሚያስረዳው ከሆነ ቻሪቲ ኮሚሽኑ ከአሁን በፊት ለእነጌታቸው በሻህውረድ በስህተት «ትረስቲ» ብሎ ደብዳቤ መጻፉን አረጋግጦ ለተፈጠረው የጽህፈት ሥራ clerical error ይቅርታ ጠይቆ እነጌታቸው በሻህ ወረድ ከአመልካችነት የዘለለ ሌላ ስያሜ ሊሰጣቸው እደማይገባ አረጋግጧዋል።
ይሁን እንጂ ቻሪቲ ኮሚሽን የተሳሳተበትን ችግር ለጊዜው ይፋ ባያደርግም እነጌታቸው በሻህውረድ «ትረስቲ» በሚል የተጻፈላቸው ደብዳቤ ቻሪቲ ኮሚሽንን ለማጭበርበር ለጠበቃቸው ለዌለርስ ግሩፕ የተሳሳተ መረጃ እና ማስረጃዎች በመስጠት ስተው በማሳታቸው መሆኑን ገልጾ፤ በዚህ ምክንያት በኮሚሽኑ እና በዌለርስ ግሩፕ መካከል ኃይለ ቃል የተሞላው ከፍተኛ መጻጻፍ እንደተደረገ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የዜና ምንጮች ለዜና ዝግጅት ክፍላችን ያጠናከረው ዘገባ ያስረዳል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ጠበቃው ዌለርስ ግሩፕ እነጌታቸው በሻህውረድ ሰበካ ጉባኤውን ከሰው ፍርድ ቤት ቢሄዱ የማያዋጣቸው መሆኑን ሕጋዊ ምክር እንደሰጣቸው ውስጥ አዋቂ የዜና ምንጮች በተጨባጭ ማስረጃ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን፤ በአሁኑ ጊዜ አማጺ ቡድኑ ወደፊትም ወደ ኃላም መሄድ የማይችል የቁም እስረኛ ሽባ ውይም አቅም የሌለው መሆኑን የተረጋገጠ ቢሆንም፤ እሁድ እሁድ ነጭ ደንኳን እየጋረደ አባላቱን እያታለለ እና ነጭ ውሽት ማሰራጨቱን እንደቀጠለበት የሚገኝ መሆኑን የዜና ወኪላችን ዘግቧል።
የዕለቱ ዜና በዚህ አበቃ
ዘጋቢ እወነት በቃሉ ነኝ ለዜና ደብረጽዮን ዘግጂት ክፍል፤ ሎንደን፡