ሰላም ወላጆች፣ አሳዳጊዎች፣ እና ቤተሰቦች፣
ከእርስዎ ጋር ግንኙነት እያደረግን ያለነው ወላጆች እና አሳዳጊዎች የተማሪዎቻቸውን ሂደት እና ክፍል ውስጥ መገኝት ለመከታተል ለሁለት አስፈላጊ መሳሪያዎች መዳረሻ እንዳላቸው ማወቃቸውን ለማረጋገጥ ነው። የመጀመሪያው መሳሪያ Parent Portal (የወላጅ ፖርታል) ሲሆን ይህም አጠቃላይ ውጤቶችን ወይም ግሬዶችን እና ክፍል ውስጥ መገኘትን ወይም አቴንዳንስን ያሳያል። ሁለተኛ መሳሪያ ደግሞ Schoology ነው፣ ይህም የተወሰኑ ግሬዶችን፣ የቤት ስራዎችን፣ ክፍሎችን፣ ወዘተ ያሳያል። እነዚህ ከወዲሁ ያዘጋጁዋቸው ነገሮች ከሆኑ፣ በጣም ጥሩ! ካልሆነ፣ ለእያንዳንዱ ከታች የተዘረዘሩ መመሪያዎች አሉ።
መጀመሪያ የወላጅ ፖርታል ላይ መመዝገብ አስፈላጊ ነው፣ ምክንያቱም ወደ Schoology ለመድረስ በወላጅ ፖርታል በኩል ማለፍ አስፈላጊ ነው። ለማዘጋጀት ከ 15-20 ደቂቃዎች ይወስዳል። ተጨማሪ ድጋፍ ካስፈለግዎት፣ እባክዎ ለመጠየቅ ነፃ ይሁኑ። በስልክ፣ በ Google Meet፣ ወይም በአካል፣ ካስፈለገ ከአስተርጓሚ አገልግሎቶች ጋር ድጋፍ ልናደርግሎት እንችላለን።