የሥሬ የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር እድሳት ላይ ውይይት ተደረገ፤
===
ጥቅምት 8 ቀን 2017 ዓ/ም፣ አዲስ አበባ
ንጋት፡ የአርሲ-ሥሬ ልማት ማህበር (ንጋት) በተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ አንኳር የሆኑ የአካባቢው ችግሮች እና መፍትሔዎችን በመለየት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
ከUN-ECA እና AAU የተገኙ በሚሊየን ብር የሚገመቱ ቁሳቁሶችን በልግስና እንዲገኙ በማስተባበር ለከፍተኛ ፪ኛ ደረጃ ት/ቤት እንዲገቡ አስተባብሯል። በቴክኒክና ሙያ፣ በትምህርት፣ በውኃ፣ በመብራት እና በመረጃ ቴክኖሎጂ ዘርፎች ፕሮፖዛል ቀርፆ ከለጋስ ድርጅቶች፣ ማህበረሰቡ፣ ተወላጆች እና ወዳጆች ጋር ወደ ትግበራ ለመግባት ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ይገኛል። ለዚህ ሥራ መቀላጠፍ ያግዝ ዘንድ በሥሬ ከፍተኛ ፪ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና መምህራን በጎ ፈቃድ ሥሬ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ከፍቷል። ማህበሩ በቅርቡ በተመሳሳይ መልኩ በአዳማ ፅ/ቤት ለመክፈት በሒደት ላይ ሲገኝ፣ በአውሮጳ እና በአሜሪካም ፅ/ቤት ለመክፈት የተወላጅ እና ወዳጆች የበጎ ፈቃድ ምላሽ እየጠበቀ ይገኛል።
ትናንት ጥቅምት 8 ቀን 2017 ዓ/ም ደግሞ በኢትዮጵያ መብራት ኃይል መሥሪያ ቤት በመገኘት በ1974 ዓ/ም የተዘረጋው የባለ እንጨት ቋሚ መስመር እድሳት ዙሪያ ጠለቅ ያለ ውይይት ተደርጓል። ንጋት ከወረዳው አስተዳደር፣ መዘጋጃ፣ እና ውኃ አቅርቦት ኃላፊዎች የተውጣጣ ልዑክ ጋር በመሆን ለ500 ተጠቃሚዎች የተዘረጋ መስመር አሁን ወደ 30,000 ለሚጠጉ ተጠቃሚዎች የተቆራረጠ አገልግሎት እንደሚሰጥ፣ ፈጠኖ ጥገና የሚሰጥ የቅርንጫፍ ማስተባበሪያ ማዕከል እንደሌለው፣ ቋዎች እየወደቁ የሰውና የእንስሳት ህይወት መጥፋት፣ የተለያዩ የቢሮ እና የቤት ማሽኖች እና ቁሳቁሶች መቃጠል፣ የተማሪዎች ውጤት መቀነስ፣ የጤና አገልግሎት መስተጓጎል፣ እስከ ኮሽም እና የአካባቢው ማህበረሰብ የመብራት ማስፋፊያ ስራዎችን ማስተጓል፣ ወደ 400 ሜትር ከፍታ ተገፍቶ የሚወጣ ውኃ አቅርቦት መቆራረጥ፣... የመብራት መቆራረጥ ችግሮችን እንዲሁም የኮንክሬት ቋሚዎች እና የሥሬ ከተማ የመብራት ቅገልግሎት ፅ/ቤት መክፈት መፍትሔዎች ዙሪያ ለኃላፊዎች ለማስረዳት እና ለመወያየት ተችሏል።
እንዲህ ዓይነት ችግሮች በአስቸኳይ የጥናት ቡድን ተልኮ ጥናት እንደሚደረግ፣ ጥናቱን መሰረት በማድረግ መስመሩን የማሻሻል ሥራ እንደሚሰራ እና ከንጋት ማህበር ጋር ቀጣይ ግንኙነት ለማድረግ መግባባት ላይ ተደርሷል።
አጋጣሚውን በመጠቀም ንጋት ከሥሬው ልዑክ ጋር ጠለቅ ያለ ውይይት አድርጓል። በውይይቱ የመረጃ ክፍተት እንዳይኖር፣ መረጃን ሰንዶ መለዋወጥ እንደሚያስፈልግ፣ የመብራት ጥናት ቡድን ሲላክ ዝርዝር መረጃዎችን በቅድሚያ ዝግጁ በማድረግ ማስተናገድ እንዲደረግ፣ ከንጋት ማህበር ጋር ያለው መልካም ግንኙነት እንዲቀጥል ጠለቅ ያለ ውይይት ተደርጓል።
ማህበራችን ንጋት፣ የሥሬና አካባቢው ማህበረሰብ፣ ተወላጆችና ወዳጆች የተጀመረው ጥረት መሬት እንዲነካ ከጎናችን እንድትሆኑ ጥሪውን ያቀርባል።
አላማችን ግልፅ፣ ቀላል እና የሚተገበር ነው፤
ብዙ የተማሩ፣ ሃብት ያካበቱ፣ በአስተዳደር እና የመንግስት ሥልጣን አሉ የተባሉ ባለቁጭት በአለም የተበተኑ ልጆች እና ወዳጆቿን በማሰባሰብ ሥሬ እና አካባቢዋን ከኢትዮጵያ ተጠቃሽ ሰላማዊ የለማች ቦታ ማድረግ ነው ።
ሰላማችን ይብዛ።
===
Discussion on Sire’s Electric Power Line Upgrade Held
October 18, 2024, Addis Ababa
Since its establishment, Nigat: Arsi-Sire Development Association (Nigat) has been dedicated to identifying key local issues and implementing solutions. Nigat has coordinated the acquisition of materials worth millions of Birr from the UN-ECA and AAU, which were used to support the high school. It has also developed proposals in areas such as technical and vocational training, education, water, electricity, and information technology, finalizing implementation plans with the help of generous organizations, the local community, natives, and supporters. To facilitate these efforts, Nigat has opened a coordinating office at Sire Secondary School, with voluntary contributions from the school’s teachers. The association is also in the process of opening an office in Adama and is awaiting support from natives and friends to establish offices in Europe and America.
On October 19, 2024, Nigat, along with a delegation from the district administration, municipality, and water supply offices, held an in-depth discussion with the Ethiopian Electricity Authority regarding the restoration of a wooden power line laid in 1974. The line, originally intended to serve 500 users, now provides intermittent service to nearly 30,000 users. The lack of a branch coordination center for quick repairs has led to power outages, collapsing power lines, loss of human and animal lives, and damage to office and household appliances. These issues have also affected student performance, disrupted health services, halted electricity expansion projects to Kosham village and nearby farming communities, and interrupted water supply systems.
After the above issues being discussed, it was agreed that an urgent study team would investigate these problems and propose solutions to improve the electricity line and address the outages. Nigat will continue its communication to ensure the implementation of the discussed solutions.
During the meeting, Nigat held further discussions with the Sire delegation team to address the information gap, emphasizing the need for better communication and detailed preparations for the study team. The importance of maintaining a strong relationship with the Nigat Association was also highlighted.
In this regard, Nigat calls on the Sire community, natives, and friends around the globe to support these efforts so that the initiatives already in progress can be successfully implemented.
Our mission is clear and actionable:
to unite the educated, wealthy, and committed administrative and governmental sectors natives, and friends of Sire scattered across the world, and to make Sire and its surrounding areas one of the most prosperous and peaceful places in Ethiopia.
May our peace flourish.
ጥር 26 ቀን 2016 ዓ/ም
ንጋት፡ የአርሲ ሥሬ ልማት ማህበር የጠቅላላ ጉባኤ የመጀመሪያ መድበኛ ስብሰባውን አዳማ፣ ሞሃመድ ኑር ህንፃ ሲኒማ ሞርሞር በተሳካ መልኩ አካሄደ። የአርሲ ስሬ ተወላጅ እና ወዳጆች ከተለያየ የኢትዮጵያ ክፍል ተሰባስበው በማህበሩ ስትራቴጂ እና መሰል ሰነዶች ላይ መክረዋል። የማህበሩን አመታዊ እቅድ እና አዳዲስ አመልካቾችን አባልነት ጉባኤው አፅድቋል።
ብዙ አመታት ተገናኝተው የማያውቁ የት/ቤት ጓደኞች በናፍቆት ሲተያዩና ለአካባቢው የተሻለ ነገ በቁጭት ሲመክሩ ማየት በዚህ አስቸጋሪ ወቅት የሚገርም ትዕይንት ሆኖ አልፏል። አካባቢው ያለውን የተማረ የሰው ሃይል፣ የተፈጥሮ ሃብት፣ የተለያየ ሃገር ተሞክሮ፣ ገንዘብ እና ቁሳቁስ በተጣና እና በተባበረ መልኩ አቀናጅቶ ይህን የተዳፈነ የተወላጁ እና ወዳጁ የተዳፈነ እሳት በሚፈለገው መልኩ ማቀጣጠል፤ በስብዕና ልዕልና፣ በትምህርት፣ በመንገድ፣ በውሃ፣ በሃይል አቅርቦት፣ በግብርና፣ በከተማ፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ ሃብት፣ በማህበራዊ አገልግሎት፣ ... በማልማት ሥሬና አካባቢዋን ከኢትዮጵያ መሰል አካባቢዎችዎች ቀደምትና ናሙና በማድረግ ሃገራዊ እና አለማቀፋዊ ግዴታችንን በተሳካ መልኩ እንወጣለን" የሚለው መርህ ይህ መንግስታዊ ያልሆነ የልማት ማህበር ዋና መነሻና የእለት እለት ህልም ነው።
“እንዴት?” ለሚለው መልስም መነሻ ሰነዶች ተዘጋጅተዋል። እነዚህን ሰነዶች እየተገበሩ ጉድለታቸውን መሙላት፣ የሁሉም ወዳጅ እና ተወላጅ ልምድን በማካፈል፣ በንቃት አስተያየት መስጠት፣ ከዚህ በፊት ለአካባቢው እበተናጥል እየተደረገ ያለውን አስተዋፅዖ በማህበሩ ስርዓት ስር በተሻለና በተሰነደ መልኩ አጠናክሮ በመቀጠል፣ ... ለነገ የማይባል ሥራ መሆኑን በአንክሮ ተመክሯል፤ ዛሬን በአብሮነት እንዲህ ካልሰራን ለልጆቻችን የተሻለ ነገ እንደማይታለም ያለፈ ዘመናችን ምስክር መሆኑም በቁጭት ተወስቷል።
የአዳማው የማህበሩ አስተባባሪ ቡድን እጅግ በሚገርም ፍጥነት እና ትጋት ጥር 26 ቀን የሚካሄደውን የማህበሩን አጠቃላይ ጉባዔ ቅድመ ዝግጅት እያጠናቀቀ ነው::
የተሰሩ ስራዎች ዘገባ ይቀርባል:: እቅድ: አዲስ አባላት ቅበላ: ስትራቴጂና ልዩ ልዩ የአሰራር መመሪያዎች በጠቅላላ ጉባዔው ይፀድቃሉ:: ናፍቆት እና የሥሬ መሻሻል ቁጭት ያንገበገባቸው ልጆች ከስሬም ሆነ ከተለያዩ ቦታዎች ይገናንኛሉ:: እንደ አባላት ጥያቄ መሰረት በቀጥታ በዩቱብ እና ፌስቡክ የማህበሩ ገፆች ስብሰባውን ለማስተላለፍ ይሞከራል::
አይቀርም::
የሥሬ የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር እድሳት ላይ ውይይት ተደረገ።
ጥቅምት 8 ቀን፣ 2017 ዓ/ም፣ አዲስ አበባ
===
ንጋት፡ የአርሲ-ሥሬ ልማት ማህበር (ንጋት) በተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ አንኳር የሆኑ የአካባቢው ችግሮች እና መፍትሔዎችን በመለየት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
ከUN-ECA እና AAU የተገኙ በሚሊየን ብር የሚገመቱ ቁሳቁሶችን በልግስና እንዲገኙ በማስተባበር ለከፍተኛ ፪ኛ ደረጃ ት/ቤት እንዲገቡ አስተባብሯል። በቴክኒክና ሙያ፣ በትምህርት፣ በውኃ፣ በመብራት እና በመረጃ ቴክኖሎጂ ዘርፎች ፕሮፖዛል ቀርፆ ከለጋስ ድርጅቶች፣ ማህበረሰቡ፣ ተወላጆች እና ወዳጆች ጋር ወደ ትግበራ ለመግባት ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ይገኛል። ለዚህ ሥራ መቀላጠፍ ያግዝ ዘንድ በሥሬ ከፍተኛ ፪ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና መምህራን በጎ ፈቃድ ሥሬ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ከፍቷል። ማህበሩ በቅርቡ በተመሳሳይ መልኩ በአዳማ ፅ/ቤት ለመክፈት በሒደት ላይ ሲገኝ፣ በአውሮጳ እና በአሜሪካም ፅ/ቤት ለመክፈት የተወላጅ እና ወዳጆች የበጎ ፈቃድ ምላሽ እየጠበቀ ይገኛል።
ትናንት ጥቅምት 8 ቀን 2017 ዓ/ም ደግሞ በኢትዮጵያ መብራት ኃይል መሥሪያ ቤት በመገኘት በ1974 ዓ/ም የተዘረጋው የባለ እንጨት ቋሚ መስመር እድሳት ዙሪያ ጠለቅ ያለ ውይይት ተደርጓል። ንጋት ከወረዳው አስተዳደር፣ መዘጋጃ፣ እና ውኃ አቅርቦት ኃላፊዎች የተውጣጣ ልዑክ ጋር በመሆን ለ500 ተጠቃሚዎች የተዘረጋ መስመር አሁን ወደ 30,000 ለሚጠጉ ተጠቃሚዎች የተቆራረጠ አገልግሎት እንደሚሰጥ፣ ፈጠኖ ጥገና የሚሰጥ የቅርንጫፍ ማስተባበሪያ ማዕከል እንደሌለው፣ ቋዎች እየወደቁ የሰውና የእንስሳት ህይወት መጥፋት፣ የተለያዩ የቢሮ እና የቤት ማሽኖች እና ቁሳቁሶች መቃጠል፣ የተማሪዎች ውጤት መቀነስ፣ የጤና አገልግሎት መስተጓጎል፣ እስከ ኮሽም እና የአካባቢው ማህበረሰብ የመብራት ማስፋፊያ ስራዎችን ማስተጓል፣ ወደ 400 ሜትር ከፍታ ተገፍቶ የሚወጣ ውኃ አቅርቦት መቆራረጥ፣... የመብራት መቆራረጥ ችግሮችን እንዲሁም የኮንክሬት ቋሚዎች እና የሥሬ ከተማ የመብራት ቅገልግሎት ፅ/ቤት መክፈት መፍትሔዎች ዙሪያ ለኃላፊዎች ለማስረዳት እና ለመወያየት ተችሏል።
እንዲህ ዓይነት ችግሮች በአስቸኳይ የጥናት ቡድን ተልኮ ጥናት እንደሚደረግ፣ ጥናቱን መሰረት በማድረግ መስመሩን የማሻሻል ሥራ እንደሚሰራ እና ከንጋት ማህበር ጋር ቀጣይ ግንኙነት ለማድረግ መግባባት ላይ ተደርሷል።
አጋጣሚውን በመጠቀም ንጋት ከሥሬው ልዑክ ጋር ጠለቅ ያለ ውይይት አድርጓል። በውይይቱ የመረጃ ክፍተት እንዳይኖር፣ መረጃን ሰንዶ መለዋወጥ እንደሚያስፈልግ፣ የመብራት ጥናት ቡድን ሲላክ ዝርዝር መረጃዎችን በቅድሚያ ዝግጁ በማድረግ ማስተናገድ እንዲደረግ፣ ከንጋት ማህበር ጋር ያለው መልካም ግንኙነት እንዲቀጥል ጠለቅ ያለ ውይይት ተደርጓል።
ማህበራችን ንጋት፣ የሥሬና አካባቢው ማህበረሰብ፣ ተወላጆችና ወዳጆች የተጀመረው ጥረት መሬት እንዲነካ ከጎናችን እንድትሆኑ ጥሪውን ያቀርባል።
አላማችን ግልፅ፣ ቀላል እና የሚተገበር ነው፤
ብዙ የተማሩ፣ ሃብት ያካበቱ፣ በአስተዳደር እና የመንግስት ሥልጣን አሉ የተባሉ ባለቁጭት በአለም የተበተኑ ልጆች እና ወዳጆቿን በማሰባሰብ ሥሬ እና አካባቢዋን ከኢትዮጵያ ተጠቃሽ ሰላማዊ የለማች ቦታ ማድረግ ነው ።
ሰላማችን ይብዛ።
===
መልዕክቱን በትክክል ኦሮሚፋ በመተርጎም ተባበሩኝ፤ የቴሌግራምን ፅሁሑፉን ወደ እንግሊዝኛ የመተርጎም እርዳታን በመጠቀም መግባባትም ይቻላል።
===
Address፡ Tel.: - +251 972 02 00 83
E-mail: - Nigatarsisire@gmail.com
Webpage: - Nigat/ንጋት: Arsi-Sire (google.com (https://sites.google.com/view/nigat/home?authuser=1))
YouTube: - Nigat: Arsi-Sire (https://www.youtube.com/channel/UCLFBwfJ7k3UXVbzQxtQUbIw)
• Office addresses: - Main Office-Akaki-Kality Sub-city, Tera Oil BLDG-306, Addis Ababa (https://www.google.com/maps/@8.8671015,38.7983062,193m/data=!3m1!1e3?entry=ttu&g_ep=EgoyMDI0MTAxNi4wIKXMDSoASAFQAw%3D%3D).፣ and Sire Coordination Office (https://www.google.com/maps/place/8%C2%B016'28.9%22N+39%C2%B029'42.4%22E/@8.274681,39.495104,773m/data=!3m1!1e3!4m4!3m3!8m2!3d8.274681!4d39.495104?entry=ttu&g_ep=EgoyMDI0MTAxNi4wIKXMDSoASAFQAw%3D%3D)
• Telegram channel: https://t.me/+x-jbYc0aRGRkMjg8
====
Discussion has hold on the renewal of Siree's electric power line.
===
Since its establishment, Nigat: Arsi-Sire Development Association (Nigat) has been dedicated to identifying key local issues and implementing solutions. Nigat has coordinated the acquisition of materials worth millions of Birr from the UN-ECA and AAU, which were used to support the high school. It has also developed proposals in areas such as technical and vocational training, education, water, electricity, and information technology, finalizing implementation plans with the help of generous organizations, the local community, natives, and supporters. To facilitate these efforts, Nigat has opened a coordinating office at Sire Secondary School, with voluntary contributions from the school’s teachers. The association is also in the process of opening an office in Adama and is awaiting support from natives and friends to establish offices in Europe and America.
On October 19, 2024, Nigat, along with a delegation from the district administration, municipality, and water supply offices, held an in-depth discussion with the Ethiopian Electricity Authority regarding the restoration of a wooden power line laid in 1974. The line, originally intended to serve 500 users, now provides intermittent service to nearly 30,000 users. The lack of a branch coordination center for quick repairs has led to power outages, collapsing power lines, loss of human and animal lives, and damage to office and household appliances. These issues have also affected student performance, disrupted health services, halted electricity expansion projects to Kosham village and nearby farming communities, and interrupted water supply systems.
After the above issues being discussed, it was agreed that an urgent study team would investigate these problems and propose solutions to improve the electricity line and address the outages. Nigat will continue its communication to ensure the implementation of the discussed solutions.
During the meeting, Nigat held further discussions with the Sire delegation team to address the information gap, emphasizing the need for better communication and detailed preparations for the study team. The importance of maintaining a strong relationship with the Nigat Association was also highlighted.
In this regard, Nigat calls on the Sire community, natives, and friends around the globe to support these efforts so that the initiatives already in progress can be successfully implemented.
Our mission is clear and actionable:
to unite the educated, wealthy, and committed administrative and governmental sectors, natives, and friends scattered across the world, to make Sire and its surrounding areas one of the most prosperous and peaceful places to live in Ethiopia.
May peace abound.
===