በእንስሳት እርባታ ዘርፍ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ለመስጠት መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
የወተት ከብት ርባታ
1.1.ቤት/ በረት
የቤቱ/በረቱ አሰራር ለእንስሳቱ ምቾት ያለዉ ሰራተኞች ለስራ ሲንቀሳቀሱና ለጽዳት አመች የሆነና በቂና ንጹህ አየር ለመዘዋወር በሚያስችል ሁኔታ መሆን ይኖርበታል፡፡
በአጠቃላይ በረቱ በአንድ ከብት ለመጠለያ 3.6 ካሬ ሜትር እና ለመዝናኛ 7.2 ካሬ ሜትር ታሳቢ ተደርጎ ይሰራል፡፡
ከከብቶች ቤት/በረት በተጨማሪ የርባታ ጣቢያዉን ስፋት መሰረት ያደረገ የጥጆች /የጊደሮች ቤት የወተት ቤት የመኖና ሳር ድርቆሽ መጋዝን መጸዳጃ ቤትና ሌሎችም ሊኖሩት ይገባል፡፡
1.2. የውስጥ ድርጅት
የእንስሳት ማቆሚያ/pen/ የመኖ መመገቢያ/feed trough/የዉሃ መጠጫ/water trough/የፍሳሽ መውረጃ /DRAINAGE/ መተላለፊያ መንገድ ወዘተ…..በመስፈርቱ መሰረት መሰራት ይኖርበታል፡፡ የከብቶች መቆሚያ/individual pen/ እስከ ፍሳሽ ማስወገጃ ቦይ ድርስ ያለዉ/ቁመት ለአንድ ላም 1.75 ሜትር ወርድ 1.20 ሜትር ሂሳብ ይሰራል፤ ወደ ፍሳሽ መዉረጃ ቦይ ያለዉ የተዳፋትነት መጠን ከ1.40 እስከ 1.60 ኢንች ነዉ፡፡ ቁመት0.50 ወርድ 0.06 ሜትር ጥልቀት 0.40 ሜትር የሆነ የመኖ መመገቢያ ገንዳ እንድሁም 0.40 ሜትር ወርድ ያለዉ የፍሳሽ ማስወገጃ ቦይ መኖር አለበት፡፡ በተጨማሪም ከቤቱ/መጠለያ ውጪ በአንድ ግዜ የጠቅላላ ከብቶቹን አንድ አስረኛ ለማጠጣት የሚያስችል ዉሃ መጠጫ ገንዳ ሊኖር ይገባል፡፡ ለወተት ከብት ርባታ አስፈላጊ የሆኑ የወተት ማለቢያ ባልድ የወተት መያዥያ ቢዶኒ የወተት ማጥለያ የጡት ማጽጃና ማድረቂያ ለስላሳ ጨርቆች አካፋ የእጅ ጋሪ ….ወ.ዘ.ተ ሊዘጋጁ ይገባል፡፡
የከብት ማድለብ
1.1.ቤት/ በረት
የቤቱ/በረቱ አሰራር ለእንስሳቱ ምቾት ያለዉ ሰራተኞች ለስራ ሲንቀሳቀሱና ለጽዳት አመች የሆነና በቂና ንጹህ አየር ለመዘዋወር በሚያስችል ሁኔታ መሆን ይኖርበታል፡፡
በአጠቃላይ በረቱ በአንድ ከብት ለመጠለያ 3.6 ካሬ ሜትር እና ለመዝናኛ 7.2 ካሬ ሜትር ታሳቢ ተደርጎ ይሰራል፡፡
ከከብቶች ቤት/በረት በተጨማሪ የርባታ ጣቢያዉን ስፋት መሰረት ያደረገ የመኖና ሳር ድርቆሽ መጋዝን መጸዳጃ ቤትና ሌሎችም ሊኖሩት ይገባል፡፡
1.2. የውስጥ ድርጅት
የእንስሳት ማቆሚያ/pen/ የመኖ መመገቢያ/feed trough/ የዉሃ መጠጫ/water trough/ የፍሳሽ መውረጃ /DRAINAGE/ መተላለፊያ መንገድ ወዘተ…..በመስፈርቱ መሰረት መሰራት ይኖርበታል፡፡ የከብቶች መቆሚያ/individual pen/ እስከ ፍሳሽ ማስወገጃ ቦይ ድርስ ያለዉ/ቁመት ለአንድ ላም 1.75 ሜትር ወርድ 1.20 ሜትር ሂሳብ ይሰራል፤ ወደ ፍሳሽ መዉረጃ ቦይ ያለዉ የተዳፋትነት መጠን ከ1.40 እስከ 1.60 ኢንች ነዉ፡፡ ቁመት0.50 ወርድ 0.06 ሜትር ጥልቀት 0.40 ሜትር የሆነ የመኖ መመገቢያ ገንዳ እንድሁም 0.40 ሜትር ወርድ ያለዉ የፍሳሽ ማስወገጃ ቦይ መኖር አለበት፡፡ በተጨማሪም ከቤቱ/መጠለያ ውጪ በአንድ ግዜ የጠቅላላ ከብቶቹን አንድ አስረኛ ለማጠጣት የሚያስችል ዉሃ መጠጫ ገንዳ ሊኖር ይገባል፡፡ አካፋ የእጅ ጋሪ ….ወ.ዘ.ተ ሊዘጋጁ ይገባል፡፡
የቁም እንስሳት ማድለብ
1.1.ቤት/ በረት
የቤቱ/በረቱ አሰራር ለእንስሳቱ ምቾት ያለዉ ሰራተኞች ለስራ ሲንቀሳቀሱና ለጽዳት አመች የሆነና በቂና ንጹህ አየር ለመዘዋወር በሚያስችል ሁኔታ መሆን ይኖርበታል፡፡
በአጠቃላይ በረቱ በአንድ ከብት ለመጠለያ እና ለመዝናኛ ታሳቢ ተደርጎ ይሰራል፡፡
ከከብቶች ቤት/በረት በተጨማሪ የቁም እንስሳቱን ብዛት መሰረት ያደረገ የመኖና ሳር ድርቆሽ መጋዝን ሌሎችም ሊኖሩት ይገባል፡፡
1.2. የውስጥ ድርጅት
የእንስሳት ማቆሚያ/pen/ የመኖ መመገቢያ/feed trough/የዉሃ መጠጫ/water trough/የፍሳሽ መውረጃ /DRAINAGE/ መተላለፊያ መንገድ ወዘተ…..በመስፈርቱ መሰረት መሰራት ይኖርበታል፡፡ የከብቶች መቆሚያ/individual pen/ እስከ ፍሳሽ ማስወገጃ ቦይ ድርስ ያለዉ/ቁመት ለአንድ ከብት 1.75 ሜትር ወርድ 1.20 ሜትር ሂሳብ ይሰራል፤ ወደ ፍሳሽ መዉረጃ ቦይ ያለዉ የተዳፋትነት መጠን ከ1.40 እስከ 1.60 ኢንች ነዉ፡፡ ቁመት0.50 ወርድ 0.06 ሜትር ጥልቀት 0.40 ሜትር የሆነ የመኖ መመገቢያ ገንዳ እንድሁም 0.40 ሜትር ወርድ ያለዉ የፍሳሽ ማስወገጃ ቦይ ማጠራቀሚያ ታንከር መኖር አለበት፡፡ በተጨማሪም ከቤቱ/መጠለያ ውጪ በአንድ ግዜ የጠቅላላ ከብቶቹን አንድ አስረኛ ለማጠጣት የሚያስችል ዉሃ መጠጫ ገንዳ ሊኖር ይገባል፡፡ አካፋ የእጅ ጋሪ ….ወ.ዘ.ተ ሊዘጋጁ ይገባል፡፡
በሰው ሰራሽ ዘዴ የእንስሳት ማዳቀል አገልግሎት
የሙያ ብቃት
በስራ መስኩ ለመሰማራት የሚፈልግ ሰው /ድርጅት/ከታወቀ ማሰልጠኛ/ተቋም እንስሳትን በሰው ሰራሽ በማዳቀል ቴክኒክ ስልጠና ያገኘ ወይም ሰለጠነ ባለሞያ ቀጠሮ የሚያሰራ መሆን አለበት፡፡
አገልግሎቱን ለመስጠት ወሳኝ የሆኑ ቋሚና አላቂ ዕቃዎች፣
ባለ አምስት ሊትር የፈሳሽ ናይትሮጅን መያዣ/liquid nitrogen container/
የማዳቃያ ገን/inseminating gun/
ቴርሞፍላስክ
የአዳቃይ ቴክኒሻያን ትጥቅ
ግሎቨና ሺዝ
ቴርሞሜትር
መቀስ
ፎርሴፕስ
የዶሮ ርባታ
የዶሮ ቤት
በአንድ የዶሮ ርባታ ቢያንስ የእንቀቁላል ጣይ ዶሮዎች ወይም የማሳደጊያ ቤት እና የታመሙ ዶሮዎች መለያ ቤት ሊኖር ይገባል፡፡ በተጨማሪም እንደርባታው ደረጃ የመኖ መጋዝን፣ ማስፈልፈያ ቤት፣ ቢሮ፣ ሊኖሩት ይችላል
ቤቱ ሲሰራ ረጅም ጎኑ የሰሜን-ደቡብ አቅጣጫን እንድከተል ተደርጎ ንፋስ በማይመጣበት አቅጣጫ በኩል ከመሬት አንድ ሜትር ከፍታ በላይ ያለው ግድግዳ በፍርግርግ እንጨት ወይም በወንፊት/mesh wire/ መሰራት አለበት፡፡
ቤቱ ሲሰራ ለአንድ ዶሮ የሚያስፈልገው የወለል ስፋት መጠን በዶሮዎች ዕድሜ ክልልና በርባታ ዓይነት/የእንቁላልና የስጋ/የሚወሰን ሲሆን፣ አንድ ካ.ሜ.ለአምስት እንቁላል ጣይ ዶሮዎች ወይም ለ7ቄቦች ወይም ለ10 የስጋ ዶሮዎች ወይም ለ10 አንድ ቀን ዕድሜ ላላቸው ጫጫተቶች ሂሳብ ይሰራል፡፡
ከሚሰሩት ቤቶች በተጨማሪ የቆሻሻ ማቃጠያ ጉድጓድ ሊዘጋጅ ይገባል፣
የውስጥ ድርጅት
በዶሮዎች ቤት የሚኖረው ውስጥ ድርጅት እንደርባታው ዓይነት ይለያያል፡-
በእንቁላል ጣይ ዶሮዎች ርባታ፡- የመኖ መመገቢያ/feeder/፣ ውሃ መጠጫ/waterer/ የእንቁላል መጣያ ሳጥን/nest/ ቆጥ/perch/ መሰብሰቢያ ቅርጫት/egg collecting basket/አስፈላጊ ሲሆኑ፣
በስጋ ዶሮዎች ርባታ፡-መኖ መመገቢያ ፣ውሃ መጠጫ፣ሲያስፈልግ፣ታርደው የሚታሸጉ ዶሮዎች የሚቀርቡ ከሆነ ለማደራጀት አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች ያስፈልጋሉ፡፡
ርባታ የአንድ ቀን ዕድሜ ባላቸው ጫጩቶች የሚጀምር ከሆነ የጫጩቶች ማሞቀያ/hoover/ግርዶሽ /chick guard/ የጫጩት መኖ መመገቢያና ውሃ መጠጫ አስፈላጊ ናቸው፡፡
ዕንቁላል በማስፈልፈል ደረጃ የሚቋቋም ርባታ ጣቢያ የእንቁላል ማስታቀፊያና ማስፈልፈያ መሳሪያ /incubator /ሊኖረው ይገባል፡፡
አሳማ ርባታ
ቤት/ በረት
የቤቱ/በረቱ አሰራር ለእንስሳቱ ምቾት ያለዉ ሰራተኞች ለስራ ሲንቀሳቀሱና ለጽዳት አመች የሆነና በቂና ንጹህ አየር ለመዘዋወር በሚያስችል ሁኒታ መሆን ይኖርበታል፡፡
በአጠቃላይ በረቱ በግሩብ ለሚኖሩ አሳማዎች ለመጠለያ፣ለመመገቢያ፣ለውሐ መጠጫ፣ለፍሳሽ ማስወገጃ እና ለመዝናኛ ታስቦ ከሌሎች በማይገናኙበት መልኩ በአመች ማቴሪያል ተከፋፍሎ መሰራት ይኖርበታል፣
የወላድ አሳማዎች ቤት ለእያንዳንዷ እናት አሳማ ከእነ ልጆቿ ታሳቢ ተደርጎ ሊሰራ ይገባል፣
የውስጥ ድርጅት
የእንስሳት ማቆሚያ/pen/ የመኖ መመገቢያ/feed trough/የዉሃ መጠጫ/water trough/የፍሳሽ መውረጃ /DRAINAGE/ መተላለፊያ መንገድ ወዘተ….. በግሩብ የሚኖሩ አሳማዎችን ታሳቢ እና እናት አሳማን ታሳቢ አድርጎ በመስፈርቱ መሰረት መሰራት ይኖርበታል፡፡ ወደ ፍሳሽ መዉረጃ ቦይ ያለዉ የተዳፋትነት መጠን ከ1.40 እስከ 1.60 ኢንች ነዉ፡፡ ቁመት0.50 ወርድ 0.06 ሜትር ጥልቀት 0.40 ሜትር የሆነ የመኖ መመገቢያ ገንዳ እንድሁም 0.40 ሜትር ወርድ ያለዉ የፍሳሽ ማስወገጃ ቦይ በተጨማሪም የቆሻሻ ማጠራቀሚያና ማቃጤ መኖር አለበት፡፡
በቆዳና ሌጦ ልማት ስራ
በቆዳና ሌጦ ስራ ለመሰማራት የምርቱን ጥራት ለመጠበቅ የሚያስችል የተሰራ መጋዘን/ማደራጃ ያስፈልጋል፣ በዚህም መሰረት፣
1. ማደራጃው የሚሰራበት ቦታ ተስምሚነት፣
· ቦታው መጠነኛ ተዳፋትነት ያለው፤
· አስተማማኝ የውሃና ኤሌትሪክ አቅርቦት፣ አንድሁም የመኪና መንገድ ያለው፣
2. ማደራጃው ለብቻው በአጥር የተከለለ መሆን አለበት፣
3. የሚሰራው ማደራጃ የሚከተሉት ክፍሎች ሊኖሩት ይገባል፣
· የእርጥብ ክፍል፣ የማጠብ፣ የማንጠፍጠፍ፣ ጨው የመቀባት፣ የቆዳና ሌጦ፣ መወጠር ስራዎች የሚሰሩበት፣
· የደረቅ ክፍል፣ በአየር የደረቁ ቆዳና ሌጦዎች፣ በጨው ታጅለው የተንጠፈጠፉ ሌጦዎች የፀረ-ተባይ ኬሚካሎችና ጨው በመደርደሪያዎች/ርብራቦች ላይ የሚቀመጡበት/የሚከማቹበት፣
4. ማደራጃው፣
· በእያንዱ ክፍል የአየር ዝውውር እንዲኖር መስኮት/ክፍተቶች መነኖር አለበት፣
· መስኮቶቹ በጥቅጥቅ ሜሽዋየር የተሸፈኑ መሆን አለባቸው፣
· ከአንዱ ክፍል ወደሌላው ክፍል የሚያስገባ የመሃል በር መኖር አለብት፣
· ከጠረጼዛዎችና ኮርቻዎች የሚወጣውን እንጥፍጣፊ/ፍሳሽ አጠራቅሞ ወደ ውጭ የሚያስወጣ በርብራብ የተዘጋ ቦይ መሰራት አለበት፡፡
5. በቆዳና ሌጦ ማደራጃዎች መሟላት ያለባቸው ቁሳቁሶች፣
· የጨው መቀበያና ማጠቢያ ጠረንጼዛ፣
· የታጠበ ቆዳና ሌጦ ማንጠፍጠፊያ ኮርቻ፣ እንድሁም በጨው የታጀለ ሌጦ ማንጠፍጠፊያ ኮርቻ፣
· በጨው ለታጀለ ሌጦ እንድሁም ለደረቀ ቆዳና ሌጦ መደርደሪያ ርብራቦች፣
· 80 ሳ.ሜ የተራራቁ የፀረ-ተባይኬሚካልና ጨው መደርደሪያዎች/ርብራቦች
· 100ኪ.ግ.ሊመዝን የሚችል ምድር ሚዛን፣
· ከጣውላ ወይም ከሲሚንቶ የተሰራ ጠረንጼዛ፣
· የቆዳ ማጠቢያ ቁመቱ 70ሳ.ሜ ርዝመት2ሜትር ወርድ 1.50 ሜትር
· የሌጦ ማጠቢያና ጨው መቀበያ ቁመቱ70ሳ.ሜ. ርዝመት 90ሳ.ሜ.ወርድ 50ሳ.ሜ የሆነ፣
· ቢላዎች፤ሞረድ፤ቡርሽና ገመድ፣
6.ሌሎች በተጨማሪ ቢሮ፣ መጸዳጃ ቤት፣ የደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ ማሶገጃ ጉድጓድ ያስፈልጋል፡፡
የእንስሳት መኖ ችርቻሮ ንግድ
የእንስሳት መኖ ችርቻሮ ንግድ የተመጣጠነ መኖ ወይም የመኖ ጥሬ እቃዎች ምርት ወይም የመኖ ተጨማሪ ንጥረ ነገሮችን እንዲሁም ወደ ንግድ ቅብብሎ ውስጥ ሚገባውን የሳር ድርቆሽ፣የአልፋአልፋ ምርት፣የዘይት ዱቄት ተረፈ ምረት፣የአገዳና የብዕር ሰብሎች ተረፈ ምረትና የጤፍ ጭድ በችርቻሮ መሸጥን የሚካትት ይሆናል፡፡
1. ማንኛውም ሰው የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ለማገኘት የሚከለቱን መሰረታዊ መስፈርቶችን አሟልቶ መገኘት ይጠበቅበታል፡-
ሀ. መኖ ወይም የመኖ ጥሬ እቃ ምርት መጫናና ማራገፊያ መደላድል እና የማከማቻ መጋዝን ሊኖረው ይገባል፣
ለ. የመኖ መጋዝን ከአእዋፍ፣አይጥና ሌሎች የእህል በል እንስሳትና ተባይ ነጻ መሆን አለበት፣
ሐ. የመኖ እና/ወይም የመኖ ጥሬ እቃ ማከማቻ መጋዝን ለክትትል እንዲያመች በቂ ብርሃን የሚስገባና ለመረማመድ ምቹ ሁኔታ ያለው መሆን አለበት፣
መ. የመኖና መኖ ጥሬ እቃዎች ምርት መደርደሪ ጣውላ ወይም ፕላስቲክ ፓሌት ላይ መደርደርና መከማቸት አለበት፣
ሠ. ፈሳሽ የመኖ ጥሬ እቃዎች ምርት ከሆነ በማይዝግና በማያፈስ የፐላቲክ በርሚል ወይም ዴፖ ውስጥ መከማቸት አለበት፣
ረ. በሚመለከተው አካል ትክክለኛነቱ በየዓመቱ የተረጋገጠ የሙቀት እና የእርጥበት መለኪያ መሳሪያ እንዲሁም የመኖ መመዘኛ ሚዛን በማከማቻ መጋዝን መኖር አለበት፣
ሰ. የመኖ ወይም የመኖ ችርቻሮ ንግድ ድርጅት ቢንስ መጋዝን ሰራተኛ በመቅጠር የቅጥር ደብዳቤውን ከብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ጥያቄ ከማመልከቻው ጋር አያይዞ ማቅረብ ይገባዋል፣
ሸ. የመኖ ወይም የመኖ ጥሬ እቃዎች ችርቻሮ ንግድ ድርጅት ፣መኖ ወይም የመኖ ጥሬ እቃ ሲቸረችር አምራቹ ተቋም ካዘጋጀው ይዘት ውጪ ማሸጊያውን በመክፈት ክብደት የመጨመር ወይም የመቀነስ፣ተጨማሪ ግብዓት የመክተት፣የመከለስ ወይም የመቀየጥ፣መያዣና ገላጭ ጽሑፍ የመለወጥ ወይም የመቀየር ስራ በፍጹም የተከለከለ ነው፡፡ በህግም የሚያስጠይቅ ነው፡፡
2. የመኖ ወይም የመኖ ጥሬ እቃ ችርቻሮ ንግድ ድርጅት የግዴታ ውል የሚፈረምባቸው መስፈርቶች (commitment paper)
ሀ. የመኖ ወይም የመኖ ጥሬ እቃ አያያዝና አጠቃቀም ስልጠና የወሰደ የሽያጭ ሰራተኛ በመቅጠር ለማሰራት የተቀጣሪውን የተሟላ ዝርዘር መረጃና የቅጥር ደብዳቤ የማቅረብ ወይም በባለቤቱ ስራውን የሚካሄድ ከሆነ ባለቤቱ በመኖ ወይም በመኖ ጥሬ እቃ አያያዝን አጠቃቀም ስልጠና የወሰደ ስለመሆኑ ማስረጃ የማቅረብ፣
ለ. የተሟለ የስራ ሪከርድና ሠነዶችን አደራጅቶ የመያዝ፣የአገልግሎቱን አሰጣጥ ሂደት የተሟላ መረጃና ለምርመራ አስፋላጊ በሚሆንበት ጊዜ ለሚመለከተው ህጋዊ አካል ግልጽ የማድረግ፣
ሐ. የመኖ ወይም ጥሬ ዕቃ ማከማቻ መጋዝን፣የመሸጫና ማሰራጫ ቦታ መሬት የግል ይም የቡድን ወይም ማህበር ወይም በኪራይ የተገኘ ስለመሆኑ አግባብነት ካለው መ/ቤት ማረጋገጫ የማቅረብ፣
2. አመልካች ከማመልከቻው ጋር የሚያቀርበው መረጃዎች
2.1 አመልካቹ ግለሰብ ከሆነ
· ባለሙያ ትምህርት እና የስራ ልምድ ማስረጃ፣
· የድርጅት ኃላፊ በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ተነሳው ጉርድ ፎቶኮፒ፣
· የቀበሌ የመኖሪያ መታወቂያ ካርድ ፎቶኮፒ፣
1.1 አመልካቹ ግለሰብ ከሆነ
· የመስራች አባላት የውክልና ሰነድ፣
· የስራ አስኪያጅ የቀበሌ/ወረዳ/ መታወቂያ ካርድ ፎቶ ኮፒ፣
· የስራ አስኪያጅ 6ወር ያልሆነው 2 ጉርድ ፎቶ፣
· የማህበሩ የመመስረቻ እና መተዳደሪያ ደንብ ዋና ቅጅዎች