ጥልን በመስቀሉ ገደለ:(2)
በመስቀሉ ለሰው ልጆች ሰላምን አደለ:(4)
በወንጌሉ ያመናችሁ/2/
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ/4/
ወሪዶ እመስቀሉ/2/
እመስቀሉ አብርሃ ለኩሉ/4/
ዕሌኒ ንግስት ሀሰሰት መስቀሎ:(2)
ዕንባቆም ነብይ ዘአንከረ ግብሮ:(4)
ሃሌ ሉያ መርሕ በፍኖት መጎሶሙ ለጻድቃን መጎስ (2) ዝንቱ መስቀል ለአዳም ዘአግብኦ ዉስተ ገነት (2)
ደስ ይበለን እልል በሉ (2)
አልቀረም ተቀብሮ ተገኘ መስቀሉ (2)
በብርሃን መላት ዓለሙን በሙሉ (2
ምን ቢተባበሩ ምንቀኞች ቢጥሩ (2)
ቅዱስ መስቀሉንም ሸሽገው ቢሰውሩ (2)
አልቻሉም ሊያጠፉት ምን ቢተባበሩ (2)
…….አዝ…….
በተራራ ተሰውሮ ለዘመናት (2)
ተጥሎ በተንኰል ተደብቆ ከኖረበት (2)
ተገለጠ እነሆ በደመራ እሳት (2)
…….አዝ…….
እሌኒ ናት ይህን ምስጢር ያስገኘችው (2)
ደመራን በጥበብ በቦታው ያስቆመችው (2)
የተነኰልን ተራራ ያስቆፈረችው (2)
…….አዝ…….
ታሪካዊ የክርስቶስ ሕያው መስቀል (2)
ይኸው ተገለጠ በክብር በግሩም ኃይል (2)
ምንጊዜም ሲያበራ እንዲህ ይኖራል (2)
መስቀል አበባ ነህ ውብ አበባ
አደይ አበባ ነሽ ውብ አበባ/2/
አ.ዝ...................//
መስቀል አበባ ተቀብሮ ሲኖር
አደይ አበባ ሥነ ሥቅለቱ
መስቀል አበባ ዕሌኒ አገኘች
አደይ አበባ ደገኛይቱ
አ.ዝ፦መስቀል አበባ ጥራጊ ሞልተው
አደይ አበባ አይሁድ በክፋት
መስቀል አበባ ጢሱ ሰገደ
አደይ አበባ መስቀል ካለበት
አ.ዝ...............//
መስቀል አበባ ወንዙ ጅረቱ
አደይ አበባ ሸለቆው ዱሩ
መስቀል አበባ አሸብርቀው ደምቀው
አደይ አበባ ላንተ መሰከሩ