ራዕይ፡-
ለአባሎቻችን ውጤታማ ጉዞ ተገቢውን ድጋፍና ምክር በመስጠት በ2025 በጠንካራ መሰረት ላይ የቆመ የህብረት ስራ ባንክ መሆን፡፡
ተልዕኮ፡-
በአማራጭ የተሞላ የገንዘብ አሰባሰብ ሂደትን በመከተል፤ አባሎቻችን ከዕቁቡ የተቀበሉትን ገንዘብ ለቁምነገርና የስራ ህይወታቸውን ሊያሻሽሉ በሚችሉ ዘርፎች ላይ እንዲያውሉ ድጋፍና ምክር እንሰጣለን፡፡
እሴቶች፡
• ታማኝነት፤
• ፍጥነት፤
• ግልጸኝነት፤
• በህብረት መስራት፤፤
መላ ዕቁብ
መግቢያ
ዘመኑ የፋይናንስና የገንዘብ ተቋማት እየተስፋፉና ስራቸውንም ከግዜ ወደ ግዜ እያዘመኑ ያሉበት ነው፡፡ ባንኮች በላቀ ፍጥነት እየተጓዙ፤ ቅርንጫፎቻቸውን እያበዙ እና በቴክኖሎጅ እየታገዙ ነገሮችን ባጠረና ቀለል ባለ መልኩ እንድንሰራ አስችለውናል፡፡ ከዚህ የተነሳ ባንኮቻችን የኪሳችን ያህል ቀርበውናል፡፡
ይህ በአሉታዊ ጎኑ ሲታይ ደግሞ ግለሰቦች በብዙ ድካምና ልፋት የሚያገኙትን ገንዘብ ለግዚያዊ ችግር (አምሮት) ሲባል በቀላሉ ወጭ እንዲያደርጉ የሚያስችል ከመሆኑም ባሻገር ገንዘብን አጠራቅሞ ለቁም ነገር ማዋልን አስቸጋሪ አድረጓል፡፡ ፡ በተጨማሪም ካለው የኑሮ ውድነትና የገንዘብ የመግዛት አቅም መውረድ ጋር ተያይዞ ገንዘብን ማጠራቀም ብቻ ሳይሆን የተጠራቀመውንም ገንዘብ ለቁም ነገር ማዋል አልተቻለም፡፡
መላ ዕቁብ ይህን ችግር በመቅረፍ እና ገንዘብን በግድ በመቆጠብ ለቁም ነገር መጠቀም እንድንችል ድጋፍና ምክርም ጭምር ሊሰጥ የሚችል ተቋም ነው፡፡ ይህም ከመደበኛው የባንኮች አሰራር በተለየ መልኩ ከአባላቱ በየሳምንቱ የሚሰበሰበውን የብር መጠን ግልጽ ዕጣ በማውጣት ባለእድለኛው ጠቀም ያለ ገንዘብ እንዲያገኝና ሁሉም አባላት ተራ በተራ ተጠቃሚ የሚሆኑበት አሰራር ነው፡፡
ከሌሎች ተመሳሳይ ተቋማት ለየት የሚያደርገን
• ዕቁቡን የሚያስተባብሩትም ሆኑ የበላይ ጠባቂ ተደርገው የተሾሙት ግለሰቦች በግላቸው ትርፋማ የሆኑ ትልልቅ ድርጅቶችን እየመሩ ያሉና በልምድም ሆነ በትምህርት የላቁ መሆናቸው፡፡
• ሁሉም የዕብ አይነቶች የሚሰበሰቡት በቀጥታ በዕቁቡ ስም በተከፈተ አካውንት የሚገባ ሲሆን የዕጣ አወጣጡም በፍጹም ግልጸኝነት በዲጅታል የታገዘ ነው፡፡
• የዕቁቡ አባላት በተለያየ ግዜ ለአስቸቋይ ብድርም ሆነ ለስራ ማስኬጅያ የሚሆን የብር እጥረት ሲገጥማቸው ከመፍትሔ ማይክሮፋይናንስ አ.ማ ብድር የሚያመቻች መሆኑ
• ለአባላቱ ውጤታማ የገንዘብ አያያዝና አጠቃቀም ላይ ያተኮረ ነጻ የባለሙያ ምክር እና የገበያ ትስስር የሚፈጥር መሆኑ
• ዕቁቡ የሚመራበትና አባላቱም የሚተገብሩት የህብረት ስምምነት ሰነድ ያለው መሆኑ
• መረጃዎችን በወቅቱ በተለያዩ አማራጮችና ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ለአባላቱ የሚያስተላልፍ መሆኑ
• የዕቁቡ አባላት ግለሰቦች ብቻ ሳይሆኑ የተለያዩ ድርጅቶችና የሃይማኖት ተማትም ጭምር ሲሆኑ አባላቱንም በከፍተኛ ጥንቃቄ የሚመርጥ መሆኑ፡፡
• ዕቁብ የደረሳቸውም ሆነ ብድር የሚወስዱ የዕቁቡ አባላት ለወሰዱት ገንዘብ አመላለስ የሚሆን አስተማማኝ ዋስና የንብረት ተያዥ እንዲያቀርቡ የሚጠይቅ ሲሆን ይህም የማህበርተኛውን ገንዘብ በአደራ ለማስተዳደር እና ከብክነት ለመጠበቅ ቁርጠኛ መሆኑ፡፡
• ይህ ዕቁብ ከ2008ዓ.ም ጀምር በስራ ላይ የቆየ ሲሆን እስከአሁን ድረስ በገንዘብ አመላለስም ሆነ አከፋፈል ምንም አይነት ቅሬታ ከአባላቱም ሆነ ከሌሎች ያልቀረበበት መሆኑ
• ዕቁቡን ሲጀመር የነበሩት አባሎች እስከአሁን ድረስ አብረው መዝለቃቸውና በባለቤትነት ስሜት በመንቀሳቀስ ከግዜ ወደ ግዜ አባላትን እያፈሩ ያሉ በመሆኑ
• በአማራጭ የተሞላ የገንዘብ አሰባሰብ ስርአት የሚከተልና ዕጣውን አባላቱ እንደአቅማቸው መጣል እንዲችሉ በተለያየ የገንዘብ አማራጮች የቀረበ መሆኑ
• በዕቁቡ ውስጥ በተለያየ ደረጃ አተዋፅኦ ለሚያደርጉ የዕቁቡ አባላት የገንዘብ ሽልማት በዕቁቡ ማጠቃለያ የሚያደርግ መሆኑ፡፡
• የሚጠበቅባቸውን ክፍያ በወቅቱ ለሚከፍሉ፤ የተበደሩትን ብድር በአግባቡ ለሚመልሱ፤ ለዕቁቡ ማደግ የጎላ ድርሻ ለሚጫወቱ ወዘተ ግልጽ በሆነ መስፈርት ተለይተው የክብርም የጥቅምም ተካፋይ የሚሆኑበት እድል ያለው መሆኑ
• የዕቁቡን የመጨረሻዎቹን ሶስት ሳምንታት ውስጥ የሚወስዱ ግለሰቦች እንደደረጃቸው የገንዘብ ጉርሻ የሚደረግላቸው ሲሆን በተጨማሪም የመጨረሻውን የሚወስደው የዕቁቡ አባል ቀጣዩን ዕቁብ በቅድሚያ እንዲወስድ የሚያደርግ መሆኑ ነገር ግን በቀጣይ የሚወስደው የገንዘብ መጠን ቀደም ሲል ሲጥል ከነበረው አይበልጥም፡፡
• አባላት በጋራ ተሰብስበው ዕጣ የሚያወጡበትና በጋራ የሚወያዩበት መድረክ በየግዜው የሚያመቻችና በአባላቱ መካከል መቀራረብን ለመፍጠር የሚተጋ መሆኑ
የመላ ዕቁብ የህብረት ስምምነት ሰነድ
እኛ የዚህ ዕቁብ አባል የሆንን እና ስማችን በዚህ ሰነድ ውል መጨረሻ ላይ በዝርዝር የተጠቀስን የዕቁብ ማህበርተኞች ከዚህ እደሚከተለው በተዘረዘረው መሰረት ተስማምተናል፡፡
1. የዕቁቡ ስያሜ መላ ዕቁብ ሲሆን ዕቁቡም ሳምንታዊ ነው
2. የዕቁቡ ቢሮ፤ አድራሻ እና ዕጣው የሚወጣበት ቦታ ሣር ቤት በሚገኘው EGST ህንጻ ቢሮ ቀጥር 301 ውስጥ ነው ፡፡
3. የአንድ ዕጣ መደብ ብር ………………….፤ ግማሽ ዕጣ ………………………፣ ዕሩብ ዕጣ ………………………. ይሆናል፡፡ ዕቁቡ የሚሰበሰበው በየሳምንቱ ቅዳሜ ነው፡፡
4. ይህ ዕቁብ ከየካቲት ………. ጀምሮ ለተከታታይ ……….. ሳምንታት ይቆያል፡፡
5. የዕቁቡ ሙሉ እጣ ብር …………………ብር ነው፡፡ግማሽ ዕጣ ደግሞ ……………… ሲሆን ዕሩብ እጣ ……………………… ብር ይሆናል፡፡
6. ዕቁቡ የሚከተለው አሰራር ሁለት ዕጣ አንድ ሽያጭ ነው፡፡
7. የመጀመሪያው ሽያጭ በ9 በመቶ የሚታሰብ ሲሆን በሂደት እየቀነሰ ይሄዳል፡፡ በተጨማሪም የሽያጩ ወለድ የሚታሰበው አባሉ ባልከፈለው የገንዘብ መጠን ላይ ብቻ ይሆናል
8. የሚሰበሰበው ብር ገቢ መሆን ያለበት ለዕቁቡ ተብሎ በአቶ ቴዎድሮስ ይልማ እና ኅሩይ ጌታቸው ስም በተከፈተው A/cc ይሆናል፡፡ዳኛውና ጸሐፊው ቀደም ብለው ገብተው የዕቁብተኛው ገንዘብ በአካውንቱ ተጠቃሎ መግባት አለመግባቱን በዕለቱ ካጣሩ በኃላ ዕጣው ዘውትር ቅዳሜ በ 9፡30 ላይ ይወጣል ፡፡ በዕለቱ ገንዘቡን ያላስገቡ በዕጣው ውስጥ አይካተቱም፡፡
9. የዕጣውን ሂደት በአካል ተገኝተው መከታተል ለማይችሉ በቀጥታ በቴሌግራም ገጻችን የምናስተላልፍ ይናል፡፡
10. ማንኛውም አባል ዕጣው ሲደርሰው ዋስ ጠርቶና ቼክ አስይዞ ክፍያው በዕለቱ ይፈጸምለታል ፡፡
11. ማንኛውም የዕቁቡ አባል ዕቁቡን ከወሰደ በኃላ መክፈል ቢያቆም ወይም ዋሶቹ ባይከፍሉ የዋስ ዋስ ይከፍላል ፡፡የዋስ ዋሶቹም የበሉ ከሆነ በሚመለከተው ክፍል በህግ ተከሰው ይከፍላሉ ፡፡
12. አንድ ዕቁብተኛ ዕጣ ወጥቶለት ዋስ ያጣ እደሆነ የከፍለውን ገንዘብ ከጠየቀ በማስፈረሚያ ደረሰኝ ፈርሞ መውሰድ ይችላል ይህንን ብር የሚወስደው በዕቁብ መጨረሻ ነው፡፡
13. አንድ ዕቁብተኛ ዋስ ከሆነ እና የተዋሰለት ሰው ሳይከፍል ቢቀር የከፈለው ክፍያ ወደ ተዋሰው ሰው ዕዳ ይዘዋወራል ፡፡
14. አንድ የዕቁቡ አባል ዕጣ ወጥቶለት ከማህበርተኛው ዋስ ያጣ እደሆነ ከውጪ የዘመኑን ግብር የከፈለ ባለ ድርጅት ወይም የዘመኑን ግብር የከፈለ የመኪና ባለቤት ሊብሬውን አሳግዶ ማስረጃ በማምጣት ዋስ ጠርቶ መውሰድ ይችላል፡፡
15. ማንኛውም ማህበርተኛ ዋስ ከሆነ በኃላ ዋስ የሆነለት ሰው ክፍያውን መክፈል ቢያቆም ገንዘቡ ለተዋሰው ስለሚዘዋወር ድርሻውን በድጋሚ መክፈል አለበት ሳይከፍል ቢቀር ዕጣው ሲወጣለት ይመለሳል ፡፡አልከፍልም ቢል በእንቢተኛነት ተከሶ ጉዳዩ ወደ ህግ ይሄዳል
16. ማንኛውም ዕቁብተኛ ዕቁብ ወጥቶለት በቂ ዋስ ጠርቶ መውሰደ ቢችልም የዕቁቡ ዳኛ እና ጸሐፊ በተጠሩት ዋሶች ካልተማመኑባቸው ዋስትናውን አንቀበልም ማለት ይችላሉ፡፡
17. አንድ ዕቁብተኛ ዕጣ ደርሶት ከወሰደ በኃላ ቢያቆምና ባለ ዕጣውም ሆነ ዋሶቹ ለመክፈል ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተው ዳኛ እና ጸሀፊው በደንቡ መሰርት ፍርድ ቤት ቀርበው ክስ ቢመሰርቱ በየቀኑ ቀጠሮ ለሄዱበት 3000 (ሶስት ሺህ ብር ) ይከፈላቸዋል፡፡ ዳኛ ወይም ጸሐፊ በቀነ ቀጠሮ ሳይቀርቡ ቢቀሩ የተወሰነው አበል ተመላሽ ይሆናል ፡፡
18. አንድ ዕቁብተኛ ዕቁብ ጀምሮ በአንዳንድ ምክንያቶች ቢያቋርጥ በዕቁባችን ደንብ እና ሕግ መሰረት መቀጫውንም ሆነ ሌላ ተገቢ ወጪ ታስቦ ቀሪው ገንዘብ ዕቁቡ ሲያልቅ ይመለስለታል ፡፡
19. ከዕቁቡ ሽያጭም የሚገኘው ገንዘብ አስፈላጊው የስራ ማስኬጃ ወጭ ከተቀነሰ በኃላ ለአባላቱ በግልጽ ይከፋፈላል፡፡
20. ከዚህ ዕቁብ የመጀመሪያ አንድ ዕጣ ብር …………………………… በዕቁቡ ስም በተከፈተው A/C ላይ በማህበር ስም ተቀማጭ ይሆንና ዕጣው በወጣ ዕለት በተለያየ ምክንያት ዕጣው ባይማላ ለባለ ዕድለኛው ሰው እያሟላን ይሰጣል፡፡
21. ዕቁቡ በተለያየ ምክንያት ገንዘብ ፈልገው ዕጣ ግን ላልውጣላቸው አባላት ለአንድ ወር የሚቆይ ብድር የሚያበድር ሲሆነ ሙሉ ዕጣ ለገቡ እስከ ብር 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ ብር)፤ ለግማሽ እጣ ለገቡ እስከ 250,000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ) ብር በዋስትና ያበድራል፡ ፡ ይህ እድል የሚመለከተው ግን በታማኝበት ሲጥሉ ላሉት ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ብድሩን የወሰዱና ቀደም ብሎ ዕቁብ የወጣለት ሰው ግን የዚህ እድል ተጠቃሚ አይሆንም፡፡
22. ይህ በህብረት ስምምነት የተመሰረተ የዕቁብ ውል ሰነድ ሁላችንም አምነንበት ከዛሬ የካቲት 14/2018ዓ.ም ጀምሮ የፀደቀ ስለሆነ ሁላችንም በጋራ ለተፈጻሚነቱ እንድንተጋ እና በመተባበር እንድንሰራበት እየጠየቅን ይህ የዕቁብ ውል ሰነድ /በፍ/ ብ/ሕ/ቁ 1675 . 1731. 2005 መሰረት በህግ ፊት የጸና ይሆናል፡፡
አድራሻ
አዲስ አበባ፣ ሣር ቤት ከፑሽኪን አደባባይ ወረድ ብሎ EGST ህንጻ ቢሮ ቀጥር 306
ስልክ +251962488546/+251911213743
ቴዎድሮስ ይልማ እና ኅሩይ ጌታቸው
ስልክ፡- 0962488546 ወይንም 0911213743
የሂሳብ ቁጥሮች
የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000476802621
ብርሃን ባንክ
1501160054902
ህብረት ባንክ
4660711365427028
አዋሽ ባንክ፡
013200028193901
አቢሲንያ ባንክ፡
225851174
ንብ ባንክ
169 SAV 2328
ዳሸን ባንክ
5611967778011