በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
" ምን ልታዩ ወጥታችኋል?
(ማቴ. ፲፩:፱)
በሃገራችን ስም አጠራራቸው ከከበሩ አባቶች አንዱ እኒህ ጻድቅ ናቸው:: ትውልዳቸው ሮም ሲሆን እግዚአብሔርን ከሚፈሩ ከአባታቸው ይስሐቅና ከእናቸው እድና የተገኙ የቅዱሳን ፍሬ ናቸው ፤ ወንድሞቹም ቴዎድሮስ እና ገብረ አምላክ ይባላሉ፡፡ የቀድሞው ስማቸው ዘሚካኤል ነበር፡፡
“አረጋዊ” የተባሉት ኢትዮጵያ ከመጡ በኋላ ነው፡፡ በእድሜ ልጅ ሲሆኑ በመንፈሳዊ ሕይወታቸውና ሥራቸው አዋቂ ስለነበሩ አረጋዊ ብለዋቸዋል፡፡
" ምን ትጠቀማላችሁ?''
፠ አባታችን አቡነ አረጋዊም የእርጅና ዘመናቸው በደረሠ ጊዜ እግዚአብሔር ወደ እርሱ በመንፈቀ ሌሊት ተገልጾ ቃልኪዳን ሰጣቸው፡፡ ይኸውም ‹‹መታሰቢያህን ያደረገ በጸሎትህም የተማመነውን ሁሉ እኔ በመላእክት ፊት ሞገስን ቧለሟልነትን እሰጠዋለሁ፤ በእውነተኛ ሀይማኖት ሁሉ የገድልህን መጽሐፍ የጻፈ፤ ያጻፈ፤ የተረጐመ እኔ ስሙን በሕይወት መጽሐፍ እጽፈዋለሁ፤ ይህ ሁሉ ላደረገም እስከ 14 ትውልድ ድረስ እምርልሀለሁ›› አላቸው፡፡
" ለምን እንደሚነግሡ ያውቃሉ?''
ከዚህም በኋላ አባታችን አልሞተም በዓመቱ "ሞትን የማይቀምሱ አሉ፡፡" ብሎ እንደተናገረው /ማቴ 16 ፥ 28/ ጥቅምት 14 ቀን 558 ዓ.ም ተሠውረዋል፡፡
ከጻድቁ አባት በረከት ይክፈለን፤
በቃልኪዳናቸው ይጠብቀን፤ አሜን፡፡
የበአሉ መርሀ ግብራት
አብረን እንዘምር
መዝሙር 1
አቡነ_አረጋዊ
አቡነ አረጋዊ ጻድቁ መነኩሴ
በኃጢአት አንዳትሞት ሕያዊቷ ነፍሴ
ጻድቁ አማልደኝ በቅድመ ሥላሴ(፪)
ከእናት ከአባት ፍቅር - - አቡነ አረጋዊ
አምላክን መርጠሀል - - አቡነ አረጋዊ
መከራ መስቀልን በእውነት ታግሰሀል
የእግዚአብሔር ቸርነት ከሞት ሰውሮሃል
አዝ
ምስጢረ መለኮት - - አቡነ አረጋዊ
በልብ ቢመላ - - አቡነ አረጋዊ
አረጋዊ ተባልክ ሣለህ ታናሽ ጨቅላ
ጸጋህ ትደርብን ትሁንልን ጥላ
አዝ
ከዳሞት ተራራ - - አቡነ አረጋዊ
ከማህሌት ከተማ - - አቡነ አረጋዊ
በጽዮን ዝማሬ ነፍስህ ብትጠማ
በዘንዶ ተጉዘህ ሰማህ ያንን ዜማ
አዝ
የህግ መምህር - አቡነ አረጋዊ
በረከት አድለን - አቡነ አረጋዊ
ከድካም ወደ ኃይል በእምነት አሻግረን
ወደ ጌታ ደስታ በምልጃህ አቅርበን
መዝሙር 2
✞አቡነ አረጋዊ✞
ኧኸ ክበር /ተመስገን/ (፪)
በዚያች ተራራ ደብረ ዳሞ
ዘንዶ በገላው ተጠምጥሞ
ከማንም በፊት የደረሰው
አረጋዊ ነው ጻድቁ ሰው
የእዚአብሔር ታማኝ አገልጋይ
በትር የሚያፀድቅ ድንጋይ ላይ
በእምነቱ ጽኑ ባሕታዊ
የአሮን ምሳሌ አረጋዊ
የጻድቁ አባት መቀመጫ
ከኃጢአት ሁሉ ነጻ መውጫ
የጽድቅ ቦታ ነች ፈጽሞ
አምሳለ ገነት ደብረ ዳሞ#አባ_አረጋዊ
መዝሙር 3
አባ አረጋዊ ሃይማኖተ ተአጽፈ
ኀበ አምደ ወርቅ(፪) ስሙ ተጽህፈ(፪)
#ትርጉም፦
አባ አረጋዊ እምነትህ ሰፋ፣
በአምደ ወርቅ ስሙ ተጻፈ
መዝሙር 4
ባርከን አባታችን
ባርከን አባታችን /ጻዲቁ መነኩሴ/(፪)አቡነ አረጋዊ
ተወከፍ(፫)ስማን ጸሎታችንን
ወረብ
አዕርገኒ ሊተ"አረጋዊ"/፪/ኀበ ደብረ ከርቤ/፪/
ወማዕከለ ማኅበር ሢመኒ መጋቤ ሢመኒ/፪/
አስራት በኩራት ማውጣት ከፈለጉ
100000000000000006 - CBE
+251-978654345678 TELEBIRR