Thank You!/Tack
ይህ ዘመን ዲጂታል የሚባሉ ነገሮች የበዙበት የዲጂታል ዘመን ነው። በዲጂታል አለም ውስጥ ደግሞ ነገሮች በዜሮ (0) እና በአንድ(፩) ይወከላሉ። እናም ታዲያ የመፅሐፉ እርዕስ 01(ዜሮ አንድ) ብር የተባለበት ምክንያት በዲጂታል ቋንቋ 0 እና 1 ባንድላይ ሲሆኑ አንድ(፩) ማለት ነው። መፅሓፉ ለኔ የመጀመሪያዬ አንድ ያልኩበት በመሆኑ፤ የመጀመሪያዬ ማለት ሲሆን፤ አንድም ዲጂታል ለማለት ነው። ባአጠቃላይ የሃገራችንን እና የአለም አቀፉን የገንዘብ እና የቴክኖሎጂ ትስስር በዘምናችን ምን እንደሚመስል ይዳስሳል።
ይህ መጸሃፍ የመጀመሪያ እትም ሲሆን በውስጡም ፩፩ ምዕራፎች ሲኖሩት እንደሚከተለው ሆነው ተዋቅረዋል።
በመጀመሪያ ካርድ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ከማስረዳት ጀምሮ ስለተለያዩ የካርድ አይነቶች እንዲሁም በተለይ ስለክፍያ ካርዶችና አይነቶቻቸው ለምሳሌ ዴቢት፣ ክሬዲት፡ የስጦታ ካርድ እና አጠቃቀማቸውን ለማስረዳት ተሞክሯል። በተጨማሪም PIN, PAN, CVC, የማብቂያ ጊዜ (Expiry date) ፊርማ እና ተዛማጅ መረጃዎች በምእራፍ ፩ እና በምእራፍ ፪ ላይ በጥልቀት ተዳሰዋል።
በምእራፍ ፫ እና ፬ ላይ ሰዎች የኤሌክትሮኒካል ገንዘብን አምነው ተቀብለው መጠቀም ከቻሉ፡ ለመጠቀም የሚያስችሉትን ከክፍያ ቴክኖሎጂ ጀርባ ስላሉ ባለድርሻ አካላት ለማሳየት ሲሆን፣ በዋናነትም ስለኢሹወር፣ አኩዋየረር፣ ካርድሆልደር፣ ነጋዴ እና ካርድ ብራንድ የተባሉትን ይጠቅሳል። ስለያንዳንዳቸው ከማስረዳት ባሻገር በመሀከላቸውም ስላለው ግንኙነት ብሎም አንዱ ከአንዱ ጋር ስለሚኖረው ተፈላላጊነትና ውል እንዲሁም ሰርተፍኬት እንዴት እንደሚሰራ ለማስረዳት ተሞክሯል። በተጨማሪ በምእራፍ ፬ ከክፍያ ቴክኖሎጂዎች ጋር በተያያዘ ስላሉ አለም አቀፍ ድርጅቶች መረጃ መስጠትና የእነሱን አስፈላጊነት ማሳየት ነው።
በምእራፍ ፭ የኢትዮጵያ የገንዘብ አመጣጥና የባንክ ታሪክን ሲዳስስ በተጓዳኝም ገንዘብ በአለም መቼ እና እንዴት እንደተጀመረ እና ዛሬ ላይ የደረስንበትን የኤሌክትሮኒካል ገንዘብ አመጣጥ ለማስረዳት ተሞከሯል። በእርግጥ በዚህ ዙሪያ በከፊል የተፃፈ ነገር ቢኖርም ይህንን ምእራፍ ይበልጥ ለማስረዳትና ከኤሌክትሮኒካል ገንዘብ ጋር ያለውን ግንኙነት ትኩረት በመስጠት የሀገራችንን ታሪክ አውድ በአንድ ምእራፍ ለማጠናቀቅ ተሞከሯል።
በምእራፍ ፮ አንባቢው በኤሌክትሮኒካል ገንዘብ ላይ ያለውን አስተሳሰብ ባለፉት ምእራፎች ከአሳደገ የኤሌክትሮኒካል ገንዘብ የፈጠረውን የካሽለስ ሶሳይቲ ምንነትና አገራዊ ጥቅም ብሎም ለደንበኛው የሚፈጥረውን ጥቅም ያስረዳል።
በምእራፍ ፯ የሚስጢራዊ ጽሁፍ አፃፃፍ ጥበብን በተመለከተ ለማስረዳት ሲሞከር አላማው ግን የኤሌክትሮኒካል ገንዘብ ላይ ከዚህ ቴክኖሎጂ መኖር የተነሳ የተፈጠረውን ተአማኒነት ለማስረዳት ነው። በዚህ ምእራፍ አንባቢው ትንሽ የሂሳብ ትምህርቱን እንዲከልስ ሲደረግ በመፅሀፉ ውስጥም በሚገኙት ሁለት ባዶ ወረቀቶች ላይ ክሪፕቶግራፊን እንዲለማመድ ይደረጋል። ይህም በአይነቱ መፅሀፉን ለየት ያደርገዋል።
በምዕራፍ ፰ ላይ ለካርዱ ባለቤት የባንክ ደንበኛነትን እውቀት ሊያሳድጉ የሚችሉ ተጨማሪ መረጃዎች ይዳሰሳሉ።
ከምእራፍ ፱ እስከ ምእራፍ ፩፩ ስለኤቲኤም እና አሰራራቸው፤ ስለክፍያ፤ ሞባይል ባንኪንግ እና ኢንተርኔት ባንኪንግ ጋር ተዛማጅ ስለሆኑ ነገሮች፤ እንዲሁም በመጨረሻ ለነዚ ሁሉ ቴክኖሎጂዎች የጀርባ አጥንት ስለሆነው ስለ ካርድ ደህንነት በስፋት እንዳሰሳልን።
በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ የካርድ ቴክኖሎጂ በተለይ ደግሞ የባንክ ካርድ ላይ ስላሉ ጉዳዮች ግንዛቤ ለማስጨበጥ እና የአለም አቀፍ ደረጃቸው ምን እንደሚመስል ለማሳየት ሲሆን፡ ተያያዥነት ያላቸውን ነገሮች ለማብራራት በመሞከር ለማንኛውም አንባቢ የባንክ ባለሙያ፣ የአይሲቲ ሰዎች በአጠቃላይ ደግሞ ሀገራዊ ፋይዳ ይኖረዋል ብዬ አምናለሁ። ይህንንም ስል ጎረቤቶቻችን ኬንያ፣ ታንዛኒያ፣ ዝምባብዌ፣ አንጎላ እና የመሳሰሉት አገሮች ያላቸውን ልምድ በተለያየ አጋጣሚ ለማወቅ ጥረት አድርጌአለሁ። በአገኘሁትም መረጃ መሰረት እነዚህና የመሳሰሉት የአፍሪካ አገሮች በክፍያ አጠቃቅም ዘዴዎች ላይ በጣም የላቀ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን የተለያዩ መረጃዎች ያሳያሉ። በተቃራኒው ደግሞ በአገራችን ላይ ምንም አይነት ሊጠቀስ ወይም ይህ ነው ሊባል የሚችል በቴክኖሎጂ የተደገፈ የክፍያ ዘዴ አለመታየቱ ይህን መጽሃፍ እንድጽፍ ዋና ምክንያት ሆኖኛል። እናም በተወሰነ ደረጃ ለተጠቃሚው ማህበረሰብ፣ ለሶፍትዌር አምራቾች እንዲሁም በዚህ አቅጣጫ ላይ ፍላጎት ላላቸው መምህራንና ተማሪዎች እንደየደረጃቸው መጠነኛ እውቀት ይሰጣል ብዬ አምናለሁ።
ይህ መጽሀፍ በዋነኛነት ሀሳቡንና ማብራሪያውን በአማርኛ ቋንቋ ጽፌ፣ ቁልፍ ቃላቱን (Technical words) ደግሞ በእንግሊኛ የፃፍኩበት ምክንያት የባንክ አሰራር አለም አቀፋዊ ይዘት ያለውና ቁልፍ ቃላቶቹ በየትኛውም አለም ባሉ ባንኮች እንዳሉ የሚጠቀሙባቸው ስለሆነ፤ እኛም እንዳሉ ልንጠቀምባቸውና ልናውቃቸው ግድ ስለሆነ ነው። በመሆኑም የነሱን ማብራሪያ ግን በቋንቋችን መፃፍ የኛ ጉዳይ ነው። ይህ አይነቱ አፃፃፍ ደግሞ እንግሊዘኛ ቋንቋቸው ባልሆኑ ሀገሮችም የተለመደ ነው። በተጨማሪም በአገራችን ነጋሪት ጋዜጣ ላይ የብሔራዊ ክፍያ ስርአትን ለመደንገግ በወጣ አዋጅ ላይ የሰፈሩትን ድንጋጌዎች እንዳሉ ለመውሰድ ተሞክሯል።
በመጨረሻም ባለችኝ ጥቂት የኢኮኖሚክስ፣ የኮምፒውተር ሳይንስ፣ የሂሳብ ግንዛቤ እንዲሁም የጽሁፍ ክህሎት ጋር አዛምጄ ታሪክም ጨምሬ ኣንድ ብያለሁ። ttps:// Ͷ�Fׄ